የአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና እስከ 2045 ድረስ አኅጉራዊ ንግድን እስከ 45 በመቶ ያሳድጋል - የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና እስከ 2045 ድረስ አኅጉራዊ ንግድን እስከ 45 በመቶ ያሳድጋል - የአፍሪካ የኢኮኖሚ  ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ

ክላቨር ጋቴቴ በአዲስ አበባ በተጀመረው የአፍሪካ ልማት ኢምፓክት ፎረም የመክፈቻ ንግግራቸው ላይ “በሁሉም አኅጉራት ያሉ አገራት ከአየር ንብረት መዛባት፣ ከጂኦፖለቲካዊ መከፋፈል እና ግጭቶች፣ ከዕዳ ተጋላጭነት መጨመር፣ ከዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት መቋረጥ እና ከፈጣን የቴክኖሎጂ ለውጥ ጋር እየታገሉ ነው” ብለዋል።

“የአፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከጊዜ ወደ ጊዜ በራሷ አቅም የአገር ውስጥ ሀብትን በማንቀሳቀስ፣ ኢንቨስትመንትን በመሳብ፣ ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪዎችን በመገንባት እና ለሚያድገው ሕዝቧ ዘላቂ የሥራ ዕድል በመፍጠር ላይ የተመሠረተ ሆኗል።” ብለዋል።

በርካታ ክልሎች የሕዝብ እርጅና እና የሰው ኃይል እጥረት እያጋጠማቸው ባለበት በዚህ ወቅት፣ አፍሪካ ከዓለም ታላላቅ ስትራቴጂካዊ ሀብቶች አንዱን የሆነውን የሰው ኃብቷን እንደ ዋነኛ አቅም መጠቀም ትችላለች ሲሉ ተናግረዋል።

ጋቴቴ አክለውም “የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና እንደ ግብርና፣ የመድኃኒት ማምረቻ፣ የአውቶሞቲቭ ማምረቻ፣ ጨርቃጨርቅ፣ ወሳኝ ማዕድናት እና ዲጂታል አገልግሎቶች ባሉ ዘርፎች ተወዳዳሪ የቀጣናዊ እሴት ሰንሰለቶችን ለማልማት፣ የግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፣ በድንበር ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እና የአፍሪካን የኢኮኖሚ መቋቋም እና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ በትውልድ አንድ ጊዜ የሚገኝ ትልቅ ዕድል ይሰጣል” ብለዋል።

የአፍሪካ ልማት ኢምፓክት ፎረም አዲስ የልማት ትብብር ሞዴልን መገንባት ላይ ያተኮረ መሆኑ የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።

ዋና ጸሐፊው በንግግራቸው ላይ ያነሷቸውን ተጨማሪ ሐሳቦች ከቪዲዮው ይመልከቱ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0