ቴህራን ውሉን ካልተቀበለች አሜሪካ ዓርብ ምሽት ኢራንን በቦምብ ትደበድባለች - ትራምፕ
16:04 11.06.2026 (የተሻሻለ: 16:14 11.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ቴህራን ውሉን ካልተቀበለች አሜሪካ ዓርብ ምሽት ኢራንን በቦምብ ትደበድባለች - ትራምፕ
የኢራን ባለሥልጣናት ወደ እሳቸው በመደወል ድብደባውን እንዲያቆሙ እንደጠየቋቸው ትራምፕ ለአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። የኢራን መንግሥት ቴሌቪዥን አንድ ከፍተኛ ምንጭን ጠቅሶ በሰጠው መግለጫ ግን፣ ከትራምፕ ጋር ግንኙነት ያደረገ ማንኛውም አካል አለመኖሩን አስታውቋል።
ከሰኔ 3 እስከ 4 ሌሊት በተከሰቱ ክስተቶች፦
▪ በአሜሪካ የዕዝ ማዕከል ትዕዛዝ መሠረት፤ አሜሪካ በኢራን ላይ ለሊት 6፡15 ጥቃት መሰንዘሯን ማዕከላዊ ዕዙ ገልጿል። በደቡባዊ ኢራን በሚገኙ በርካታ ከተሞች ላይ የፍንዳታ ድምፆች መሰማታቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡
▪ የኢራን እና የአሜሪካ ኃይሎች በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ላይ ተጋጭተዋል። በቀሽም እና ሄንጋም ደሴቶች ላይ ፍንዳታዎች መከሰታቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ጠቁመዋል፡፡
▪ ቴህራን በአሜሪካ ጥቃቶች ምክንያት የሆርሙዝ ሰርጥን በነዳጅ ጫኝ መርከቦች እና በንግድ መርከቦች ላይ ዘግታለች፡፡
▪ ኢራን በቀጣናው የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችን እና በባሕሬን የሚገኘውን የአሜሪካ አምስተኛ የባሕር ኃይልን ጨምሮ 18 ኢላማዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን የኢራን አብዮታዊ ዘብ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X