ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ«5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች» ተነሳሽነት ታሪካዊ የምዝገባ ምዕራፍ ስኬትን አበሰሩ

ሰብስክራይብ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ«5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች» ተነሳሽነት ታሪካዊ የምዝገባ ምዕራፍ ስኬትን አበሰሩ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በሦስት ዓመታት ውስጥ ለማሳካት የታቀደውን ግብ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማሳካት መቻሉንና ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ 5,005,146 ሰልጣኞች መመዝገባቸውን ይፋ አድርገዋል።

በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ፣ በመረጃ ትንተና፣ በአንድሮይድ ሶፍትዌር ልማት እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ ትምህርቶች ከተመዘገቡት ሰልጣኞች መካከል ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ሥልጠናውን ማጠናቀቃቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ይህ ስኬት የሕዝባችንን ቁርጠኝነት እና ወሰን የሌለው አቅም ማረጋገጫ መሆኑን ገልጸዋል።

↗ እስከ ነሐሴ 2018 ዓ.ም. ድረስ የሰልጣኞችን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ አዲስ ብሔራዊ ግብ መቀመጡን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ወጣት ተማሪዎች መጪውን የክረምት ወቅት በዋዛ ከማሳለፍ ተቆጥበው ሙሉ በሙሉ በነጻ የሚሰጠውንና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያለውን ይህንን ሥልጠና በመውሰድ የዲጂታል መሪዎች እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0