ታንዛኒያ በአነስተኛ እና በትላልቅ ደረጃ በሚገነቡ የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ አለባት - ባለሙያ

ሰብስክራይብ

ታንዛኒያ በአነስተኛ እና በትላልቅ ደረጃ በሚገነቡ የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ አለባት - ባለሙያ

ይህ እርምጃ በውኃ ኃይል ላይ ያለውን ጥገኝነት በመቀነስና የኢንዱስትሪ እንዲሁም የማዕድን ዘርፎችን በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ፣ በቀን 24 ሰዓት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት እንዲኖር ሊያደርግ እንደሚችል የታንዛኒያ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ አሊ ማሱቢ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ከሩሲያው ሮሳቶም ኩባንያ ጋር የሚደረገው ትብብር ከፍተኛ ቴክኖሎጂዎችን እና ሰፊ ልምዶችን ወደ ታንዛኒያ ሊያመጣ የሚችል ሲሆን፤ ይህም ለአገሪቱ በኒውክሌር ኢንዱስትሪ ውስጥ “ትልቅ ዕድል” እንደሆነ ጠቁመዋል።

ታንዛኒያ ያላትን እጅግ ከፍተኛ የዩራኒየም ክምችት እና ከሩሲያ ጋር የምታከናውናቸውን የጋራ ፕሮጀክቶች በመጠቀም ራሷን የቀጣናው የኢነርጂ ማዕከል ማድረግ እንደምትችልና ይህም በአኅጉሪቱ እየጨመረ ከመጣው የኒውክሌር ኃይል ፍላጎት አንጻር በመላው አፍሪካ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እና የጂኦፖለቲካዊ ተፅዕኖ እንድታገኝ ያስችላታል ሲሉ ተናጋሪው አፅንዖት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0