የሩሲያና ታንዛኒያ የዩራኒየም ፕሮጀክት ምስራቅ አፍሪካዊቷን አገር በዓለም አቀፍ የኢነርጂ ውሳኔ ሰጪ አገራት ተርታ ያሰልፋታል - ባለሙያ
የሩሲያና ታንዛኒያ የዩራኒየም ፕሮጀክት ምስራቅ አፍሪካዊቷን አገር በዓለም አቀፍ የኢነርጂ ውሳኔ ሰጪ አገራት ተርታ ያሰልፋታል - ባለሙያ
ታንዛኒያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የዩራኒየም ፍላጎት 4 በመቶ ያህሉን ያቀርባል ተብሎ በሚጠበቀው የኤምኩጁ ሪቨር ፕሮጀክቷ ወደ ዓለም አቀፉ መድረክ ብቅ እያለች መሆኑን የታንዛኒያ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ አሊ ማሱቢ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
እንደ ማሱቢ ገለጻ ከሆነ፤ ይህ ዕድገት ለታንዛኒያ በርካታ ዋና ዋና ጥቅሞችን ያስገኛል፦
ከፍ ያለ ዓለም አቀፋዊ ደረጃ፦ ይህ ፕሮጀክት ታንዛኒያን ከተራ ማዕድን ላኪነት ወደ ኑክሌር ኃይል ጥገኝነት ላላቸው አገራት ወሳኝ አጋርነት ያሸጋግራታል።
ስትራቴጂካዊ ተፅዕኖ (ተደራዳሪነት)፦ ታንዛኒያ በዓለም አቀፉ የዩራኒየም ምርት ላይ ከፍተኛ ድርሻ በመያዝ፣ በዓለም አቀፍ የኢነርጂ ዲፕሎማሲ እና ድርድር ላይ ጉልህ ተፅዕኖ እና ጠንካራ ድምፅ ታገኛለች።
ከዓለም አቀፋዊ አዝማሚያዎች ጋር መጣጣም፦ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣ ሲሆን ለዚህም በዋነኝነት ምክንያት የሆነው የሰውሰራሽ አስተውህሎት እና የላቁ የኮምፒውተር ቴክኖሎጂዎች መስፋፋት ነው፤ የኑክሌር ኃይል ደግሞ እነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት እጅግ አስተማማኝ መፍትሔ ሆኖ እየወጣ በመሆኑ፣ ታንዛኒያን በዚህ የሽግግር ወቅት ውስጥ ቁልፍ ተዋናይ ያደርጋታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X