ትምህርት ሚኒስቴር ለቅድመ አንደኛ እስከ መካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች የተመጣጠነ ምገባ ፕሮግራም እንዲተገብር ግዴታ የሚጥል ረቂቅ አዋጅ ቀረበ
20:41 05.06.2026 (የተሻሻለ: 20:44 05.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ትምህርት ሚኒስቴር ለቅድመ አንደኛ እስከ መካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች የተመጣጠነ ምገባ ፕሮግራም እንዲተገብር ግዴታ የሚጥል ረቂቅ አዋጅ ቀረበ
ሕጉ አሳሳቢ ነው የተባለውን የመቀንጨር ችግር ለመፍታት በ13 ሚኒስቴር መስሥሪያ ቤቶች ላይ ከፍተኛ ግዴታ የሚጥል ነው መባሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ አካላቸው ሀገራት ተርታ የምትሰለፈው የተስተካከለ እና የተመጣጠነ ምግብ ያገኘ ትውልድ መፍጠር ስትችል እንደሆነ አዋጁ አመልክቷል።
በኢትዮጵያ 40 በመቶ (6.6ሚሊዮን ) የሚሆኑ ህጻናት የቀነጨሩ እንደሆኑ በ2018 ዓ.ም ይፋ የተደረገው የጤናና የሥነ-ሕዝብ ዳሰሳ ጥናት ያመለክታል።
⏭ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጅ ዙሪያ በስፋት ከተወያየ በኋላ ለጤና ማኅበራዊ ልማት ባሕልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ መርቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X