የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ የጤና ሚኒስትሮች በኢቦላ ወረርሽኝ ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂዱ ነው

© telegram sputnik_ethiopiaየምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ የጤና ሚኒስትሮች በኢቦላ ወረርሽኝ ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂዱ ነው
የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ የጤና ሚኒስትሮች በኢቦላ ወረርሽኝ ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂዱ ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.05.2026
ሰብስክራይብ

የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ የጤና ሚኒስትሮች በኢቦላ ወረርሽኝ ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያካሂዱ ነው

ከሰኞ እስከ ማክሰኞ በበይነመረብ አማካኝነት የሚካሄደው ይህ ስብሰባ፤ በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኡጋንዳ የተቀሰቀሰውንና አሁንም በቀጠለው የኢቦላ ወረርሽኝ ላይ ለመምከር እንዲሁም የቀጣናውን የጋራ የመከላከል አቅም ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ መሆኑን የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ስብሰባው የበሽታውን ስርጭት ለመግታት በቀጣናው ደረጃ እንዲወሰዱ በቀረቡ የድርጊት መርኃ-ግብሮች ላይ ይመክራል።

የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ ሴክሬተሪያት የአስቸኳይ ጊዜ ስብሰባዎችን ከማዘጋጀት ጀምሮ ለኢቦላ ክትባቶች እና ሕክምናዎች የሚሆኑ ደንቦችን እስከ ማዋሃድ ድረስ ያሉ የቀጣናዊ ቅንጅት ሥራዎችን እያጠናከረ እንደሚገኝም በመግለጫው ተጠቁሟል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0