ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከ7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ጋር የተያያዙ ችግሮችና ክስተቶችን በፍጥነት ለመፍታት የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ መስጫ ሥርዓት ይፋ አደረገ

© telegram sputnik_ethiopiaብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከ7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ጋር የተያያዙ ችግሮችና ክስተቶችን በፍጥነት ለመፍታት የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ መስጫ ሥርዓት ይፋ አደረገ
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከ7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ጋር የተያያዙ ችግሮችና ክስተቶችን በፍጥነት ለመፍታት የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ መስጫ ሥርዓት ይፋ አደረገ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.05.2026
ሰብስክራይብ

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከ7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ጋር የተያያዙ ችግሮችና ክስተቶችን በፍጥነት ለመፍታት የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ መስጫ ሥርዓት ይፋ አደረገ

ቦርዱ ዜጎች ከምርጫው ጋር የተያያዙ ማናቸውንም መስተጓጎሎች፣ የፀጥታና የሐሰት መረጃ ችግሮች እንዲሁም በማንኛውም መራጭ ላይ የሚደርሱ ማስፈራራቶችና ትንኮሳዎችን ደኅንነቱ በተጠበቀ መንገድ ሪፖርት የሚያደርጉበት ሥርዓት መዘርጋቱን አስታውቋል።

ሰላማዊ፣ ግልጽና ተዓማኒነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድ ታስቦ የተዘጋጀው ይህ ሥርዓት፤ ቦርዱና የሚመለከታቸው የፀጥታና የሕግ አካላት መረጃዎችን አስቀድመው በማግኘት ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ ለማገዝ የተዘጋጀ ነው።

ማንኛውም ዜጋ፣ የምርጫ ታዛቢ፣ የፖለቲካ ፓርቲና ምርጫ አስፈጻሚ በምርጫ ጣቢያዎች አካባቢ ምርጫን የሚያውክ ወይም ግጭት ሊቀሰቅስ የሚችል አጠራጣሪ ድርጊት ሲመለከት ወዲያውኑ ጥቆማ መስጠት እንደሚችል ቦርዱ ገልጿል።

በዚህም በነፃ የስልክ መስመር 6214 ወይም በ7555 የአጭር ጽሑፍ መልዕክት ቁጥር የሚደርሱትን ጥቆማዎች በማረጋገጥ በቅንጅት አፋጣኝ ዕርምጃ እንደሚወሰድ አመልክቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0