የዚምባብዌ የትንባሆ ገበሬዎች ደኖችን ለመታደግ የማገዶ እንጨትን በፀሐይ ማድረቂያዎች እየተኩ ነው

ሰብስክራይብ
የዚምባብዌ የትንባሆ ገበሬዎች ደኖችን ለመታደግ የማገዶ እንጨትን በፀሐይ ማድረቂያዎች እየተኩ ነው

የማታቤሌላንድ የትንባሆ ገበሬዎች ከባሕላዊው የትንባሆ ማድረቅ ሂደት ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የደን ጭፍጨፋ ለመግታት፤ በማገዶ እንጨት ወይም ከሰል ፋንታ የፀሐይ ብርሃን ማድረቂያ ዘዴን ተግባራዊ እያደረጉ መሆናቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

‘ማሩላ ባርን’ የተሰኘውና ግልጽ በሆነ የፕላስቲክ ቁስ የታጠረው የማድረቂያ ክፍል፤ ሙቀትን አምቆ በመያዝ ቅጠሎቹን ከዝናብ የሚከላከል ሲሆን እንጨት ማቃጠል ሳያስፈልግ ትንባሆው በተፈጥሯዊ አየር እንዲደርቅ ያስችላል።

ይህ አሠራር በአሁኑ ወቅት 395 ገበሬዎች ተግባራዊ እያደረጉት ይገኛሉ። አንዳንድ ገበሬዎች የአየር ዝውውር እጥረት ችግር እንዳለበት ቢገልጹም፤ አሠራሩ የማምረቻ ወጪን የሚቀንስና የምርቱን ጥራት የሚያሻሽል መሆኑተጠቁሟል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0