የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኡጋንዳ የስታንዳርድ ጌጅ ባቡር ፕሮጀክት የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባ - ሚኒስቴር
13:19 31.05.2026 (የተሻሻለ: 13:24 31.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኡጋንዳ የስታንዳርድ ጌጅ ባቡር ፕሮጀክት የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባ - ሚኒስቴር
የአፍሪካ ልማት ባንክ በአጠቃላይ 3.15 ቢሊዮን ዶላር ይፈጃል ተብሎ ለተገመተው የሀገሪቱ የ326 ኪሎ ሜትር የስታንዳርድ ጌጅ ባቡር ፕሮጀክት ጊዜያዊ የ650 ሚሊዮን ዶላር በጀት መመደቡን የኡጋንዳ ገንዘብ ሚኒስቴር አረጋግጧል።
የፋይናንስ ድጋፍ ውሳኔው የተገለጸው፤ በብራዛቪል በተካሄደው የባንኩ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በባንኩ ግዜያዊ ምክትል ፕሬዚዳንት አብዱል ካማራ አማካኝነት ነው።
የመጨረሻው የፋይናንስ ስምምነት ዝግጅት የባንኩ ልዑክ በሚቀጥለው ወር በሚያካሄደው ግምገማ ላይ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
እ.ኤ.አ በ2024 ለቱርኩ ያፒ መርከዚ ኩባንያ የተሰጠው ይህ የባቡር መስመር ዝርጋታ፤ በኬንያ የመተላለፊ መስመር ላይ ጥገኛ ለሆነችው እና ባሕር በር ለሌላት ኡጋንዳ የወደብ ማጓጓዣ ወጪን ለመቀነስና የጭነት እንቅስቃሴን ለማፋጠን ያለመ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X