የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አድሏዊነት አጠራጣሪ አይደለም - ኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ
09:31 31.05.2026 (የተሻሻለ: 11:14 31.05.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አድሏዊነት አጠራጣሪ አይደለም - ኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ
የፍትሕ ተቋሙ በኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ጡንቻ ስር ነው የሚሉት የሕግ ባለሙያ እና ተመራማሪው መታገስ ውለታው ናቸው፡፡
በሰብዓዊ ጥሰት፣ ሉዓላዊነትን በመጋፋት እና በጣልቃ ገብነት ተወዳዳሪ የሌላቸው ምዕራባውያን በፍርድ ቤቱ ሲጠየቁ አይታይም ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"ምዕራባውያን ራሳቸውን እንደ ሰብዓዊ መብት ተሟጋች አድርገው ሲቆጥሩ ይታያል፤ ነገር ግን...አንዲትን ሀገር ጠቅልሎ የመያዝ፣ በሌላ ሀገር ጣልቃ ገብቶ ከፍተኛ ጉዳት የማድረስን ነገር ከምዕራባውያን በላይ የሚፈጽመው የለም።...በትክክል የሰብዓዊ መብት አስከባሪ ናቸው ወይ? ካልን አይደሉም። ጥሰቱ በእነሱ ይብሳል፤ ሲጠየቁ ግን አይታይም። ስለዚህ አድልዎ አለ የሚለው ነገር ምንም ጥርጥር የለውም።"
ፍርድ ቤቱ አቅም ያላቸውን አይደፍርም የሚሉት ባለሙያው፤ በአብዛኛው ትኩረቱን አፍሪካ ላይ የሚያደርገው፤ የአኅጉሪቱ ሀገራት የዓለም አቀፍ ግንኙነቱን ተጽዕኖ መቋቋም የሚያስችላቸው ደረጃ ላይ ባለመሆናቸው እንደሆነ ተናግረዋል።
"ዓለም አቀፍ ሕግ አሁን በዋናነት የጉልበተኞች ሕግ ሆኗል ማለት ነው።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X