ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ለምዕራባውያን ወንጀሎች ከለላ እና የፖለቲካ ማስፈራሪያ መሣሪያ ነው - ፍልስጤማዊ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ለምዕራባውያን ወንጀሎች ከለላ እና የፖለቲካ ማስፈራሪያ መሣሪያ ነው - ፍልስጤማዊ ባለሙያ
ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ለምዕራባውያን ወንጀሎች ከለላ እና የፖለቲካ ማስፈራሪያ መሣሪያ ነው - ፍልስጤማዊ ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.05.2026
ሰብስክራይብ

ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ለምዕራባውያን ወንጀሎች ከለላ እና የፖለቲካ ማስፈራሪያ መሣሪያ ነው - ፍልስጤማዊ ባለሙያ

አይሲሲ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የእስራኤልንና የምዕራባውያን ሀገራትን ተጠያቂነት ወደ ጎን በመተው የአፍሪካ መሪዎችን በመክሰስ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረጉን የሕግ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያው ዶክተር ሳላህ አብድ ኤል-አቲ

ለስፑትኒክ ገልጸዋል።

“ፍርድ ቤቱ የጦር ወንጀል ፈጽመዋል በሚል የአፍሪካ መሪዎችን በማሳደድ ላይ ይበረታል። ነገር ግን የእስራኤል ወረራ ወንጀሎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ይዘገያል እንዲሁም በእስራኤል እና በሌሎች የምዕራባውያን ሀገራት ለሚፈጸሙ የጦር ወንጀሎችና የዘር ማጥፋት ድርጊቶች ከለላ እየሰጠ ይገኛል።”

ፍርድ ቤቱ አድሏዊ ፍትሕን የሚያራምድ የፖለቲካ ማስፈራሪያ መሣሪያ ሆኗል ሲሉም አክለዋል። አሜሪካ፣ እስራኤል እና በርካታ የአውሮፓ ኅብረት ሀገራት በሚከተለው ድርብ መስፈርት ምክንያት በፍርድ ቤቱ የማይነኩ ሆነው ቀጥለዋል።

እውነታው ይህ ቢሆንም ፍልስጤማውያን በመርህ ደረጃ አይሲሲን ጨምሮ ወደ ዓለም አቀፍ የፍትሕ ተቋማት ፊታቸውን ማዞር ከመቀጠል ውጪ ሌላ አማራጭ የላቸውም ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0