- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የደቡባዊው ዓለም የኃይል ሽግግርና አፍሪካ በባለብዙ ዋልታ ዓለም ውስጥ

የደቡባዊው ዓለም የኃይል ሽግግርና አፍሪካ በባለብዙ ዋልታ ዓለም ውስጥ
ሰብስክራይብ
''አፍሪካ በዚህ መልቲፖላር ወርልድ እንቅስቃሴ ውስጥ የቻይናንና የሩሲያን እጅና ትከሻ ተደግፋ በርታ መስራት መቻል አለባት። ምዕራባውያን ጦርና ታንክ ሳይልኩ በሚዲያቸው፣ በእርዳታቸውና በብድራቸው የእጅ አዙር ቅኝ ግዛትን በሚያራምዱበት በዚህ ዘመን፣ አፍሪካ ራሷን ማጠናከር ይኖርባታል'' ሲሉ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንታኝ ሸዋፈረው ሽታሁን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቻይና ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ ነው፣ በሞስኮ እና በቤጂንግ መካከል የሚገነባው የተቀናጀ አጋርነት እንዲሁም አዲስ ባለብዙ ዋልታ ዓለምን ለመፍጠር የሚደረገው ሽግግር ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ሽግግርና ለደቡባዊ ዓለም ሀገራት ምን ዓይነት መዋቅራዊ ዕድሎችንና አማራጮችን ይዞ ይመጣል? ስንል የፖለቲካል ኢኮኖሚ ተንታኝ ሸዋፈረው ሽታሁን ጋር ሰፊ ቆይታን አድርገናል።

በክፍል ሁለት ደግሞ አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ ያላትን የቋሚ መቀመጫ ውክልና ማጣት ታሪካዊ ዳራን በመፈተሽ፣ ጉዳዩ ለአፍሪካ የሚደረግ ‘ችሮታ’ ሳይሆን ታሪካዊ በደልን የማረም የዕዳ ክፍያ ስለመሆኑ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት መምህርና የሕግ ባለሙያ ከሆኑት ከአቶ መታገስ ውለታው ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
አዳዲስ ዜናዎች
0