የሩሲያው ሮስጂኦሎጂያ በማሊ የማዕድን ፍለጋ ጀመረ

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያው ሮስጂኦሎጂያ በማሊ የማዕድን ፍለጋ ጀመረ
የሩሲያው ሮስጂኦሎጂያ በማሊ የማዕድን ፍለጋ ጀመረ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 17.05.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያው ሮስጂኦሎጂያ በማሊ የማዕድን ፍለጋ ጀመረ

የሩሲያ የኢነርጂ ሚኒስትር ሰርጌ ትሲቪሌቭ በካዛን ፎረም በተካሄደው በሁለትዮሽ የበይነ-መንግሥታት የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ማጠቃለያ ላይ ፤ ይህ የመንግሥት የጂኦሎጂ ኩባንያ የማሊን የማዕድን ሀብቶች ለመፈተሽ እና መልሶ ለመገምገም የሚያስችለውን የሁለት ዓመት ፕሮግራም ጀምሯል ሲሉ አስታውቀዋል።

እ.ኤ.አ በ2025 በተካሄደው የመጀመሪያው የሁለቱ አገራት የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ የተስማሙበት ይህ ፕሮግራም፣ የአገሪቱን ሙሉ የጂኦሎጂካል ካርታ ለማዘጋጀት ያለመ ነው።

“ይህ ፕሮግራም ይበልጥ እንደሚራዘም ተስፋ እናደርጋለን። በመንግሥትም በኩል ድጋፍ አለው። በዚህም የተነሳ የማዕድን ሀብት መሠረቱን ዝርዝር መግለጫ ማግኘት እንችላለን” ሲሉ ፂቪሌቭ ተናግረዋል።

ሥራው፣ ከፍተኛ የተፈጥሮ ሀብት እንዳላት በሚታመነው ማሊ ላይ ያለውን የኢንቨስትመንት ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳድገው የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ፕሮጀክቱ ብሔራዊ የዲጂታል ጂኦሎጂካል መድረኮች እንዲፈጠሩ መንገድ ሊከፍት እንደሚችልም አክለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0