የጋና ኢኮኖሚ በየካቲት ወር እጥፍ አቅራቢያ ማደጉን የጋና ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopiaየጋና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እ
የጋና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.05.2026
ሰብስክራይብ
የጋና ኢኮኖሚ በየካቲት ወር እጥፍ አቅራቢያ ማደጉን የጋና ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ

የጋና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እ.አ.አ በየካቲት 2026 ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 7.7 በመቶ ዕድገት አሳይቷል። ይህም በየካቲት 2025 ከነበረው 3.9 በመቶ ከፍተኛ ጭማሪ የታየበት ሲሆን፤ ለዚህ ውጤት በኢንዱስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፎች የተመዘገቡት ጠንካራ ስኬቶች ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን የስታትስቲክስ ቢሮ ዋና ባለሙያ አልሃሰን ኢድሪሱ ገልጸዋል።

◻ ኢንዱስትሪ - በማዕድን፣ በማምረቻ እና በኤሌክትሪክ ምርት ዘርፎች በታየው መነቃቃት ምክንያት ከ2.8 በመቶ ወደ 9.6 በመቶ ከፍ ብሏል።

◻ አገልግሎት - ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ፋይናንስ፣ ንግድ እና ጤና ከ4.4 በመቶ ወደ 7.4 በመቶ አድጓል።

◻ ግብርና - በአንጻሩ የሰብል፣ የከብት እርባታ እና የደን ልማት ሥራዎች ዝቅተኛ እድገት በማሳየታቸው፤ ከ9.4 በመቶ ወደ 3.8 በመቶ ዝቅ ብሏል።

አዲስ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ በተደረገ ማሻሻያ የጥር ወር የኢኮኖሚ ዕድገት መጀመሪያ ከተገለጸው 7.5 በመቶ ወደ 6.1 በመቶ በመቶ ዝቅ እንዲል ተደርጓል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0