ዚምባብዌ በዚግ ምንዛሬ ‘በትክክለኛው አቅጣጫ ላይ ትገኛለች’ - የኢኮኖሚ ተንታኝ
18:14 10.05.2026 (የተሻሻለ: 18:24 10.05.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዚምባብዌ በዚግ ምንዛሬ ‘በትክክለኛው አቅጣጫ ላይ ትገኛለች’ - የኢኮኖሚ ተንታኝ
ዚምባብዌ ከአሜሪካ ዶላር ወደ ሀገር ውስጥ መገበያያ ገንዘብ ‘ዚምባብዌ ጎልድ’ (ዚግ) እያደረገችው ያለችው የሂደት ሽግግር፣ የፋይናንስ ሉዓላዊነትን ለማጠናከር እና የኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማምጣት የተወሰደ አዎንታዊ እርምጃ መሆኑን የቢዝነስ ስትራቴጂ ባለሙያ እና የ‘ኤአይ አፍሪካ ኢኒስቲትዩት’ ሊቀመንበር ዴኒስ ማጋያ ለሰፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
ባለሙያው ሲያብራሩም “እያንዳንዱ ሀገር የራሱን ዕድል በራሱ ለመወሰን እና የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ዕቅዶቹን በዚያው ልክ ለማስተካከል የፋይናንስ ሉዓላዊነት ያስፈልገዋል” ብለዋል።
ዚምባብዌ አዲሱን የመገበያያ ገንዘቧን ተግባራዊ ለማድረግ ስላሳለፈችው ተሞክሮ የበለጠ ለመረዳት ቪዲዮውን ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X