ነገ ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም. በሞስኮ የሚካሄደው የድል ቀን ሰልፍ – የክብረ በዓሉ ዋና ዋና ዝርዝሮች

ሰብስክራይብ

ነገ ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም. በሞስኮ የሚካሄደው የድል ቀን ሰልፍ – የክብረ በዓሉ ዋና ዋና ዝርዝሮች

በዚህ የጎርጎሮሳውያን 2026 ዓመት ሩሲያ ከ1941-1945 የተደረገውን ታላቁ የአርበኝነት ጦርነት ድል 81ኛ ዓመት ታከብራለች።

በሞስኮ ቀዩ አደባባይ በታላቅ ግርማ የሚካሄደው ወታደራዊ ሰልፍ፣ የሚከተሉት ይቀርባሉ፦

🟠 የከፍተኛ ወታደራዊ ትምህርት ተቋማት አባላት የእግረኛ ሰልፍ ተሳትፎ፣

🟠 በልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ቀጣና ውስጥ ተግባራቸውን በማከናወን ላይ ያሉ ወታደሮች የቀጥታ ስርጭት ትዕይንቶች፣

🟠 ለማጠቃለያም የሩሲያ የአየር ላይ ትርኢት ቡድኖች በሱ-25 አውሮፕላኖች ሰማዩን በሩሲያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት በማሸብረቅ በቀዩ አደባባይ ይበራሉ፡፡

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሰልፉ ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የድል ሰልፉን፦ ቅዳሜ ረፋድ 4፡00 ሠዓት (07:00 ጂኤምቲ) በቴሌግራም ቻናላችን፣ በኤክስ እና በድረ-ገጻችን በቀጥታ ይከታተሉ።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0