ጋቦን የመንግሥት ሠራተኞች በየሳምንቱ አርብ አፍሪካዊ የባሕል አልባሳትን እንዲለብሱ አዘዘች
17:17 08.05.2026 (የተሻሻለ: 17:41 08.05.2026)
© Sputnik
ሰብስክራይብ
ጋቦን የመንግሥት ሠራተኞች በየሳምንቱ አርብ አፍሪካዊ የባሕል አልባሳትን እንዲለብሱ አዘዘች
ወንድ ሠራተኞች የሚከተሉትን መልበስ ይችላሉ፦
▫ ከአፍሪካ ጨርቃጨርቅ የተሠራ ሱሪና ሸሚዝ (ያለ ከረባት) ከሽፍን ጫማ ጋር፣
▫ ባለ ሁለት ተካፋይ የአፍሪካ ጨርቃጨርቅ ልብስ (ሱፍ)፣
▫ ከአፍሪካ ጨርቃጨርቅ፣ ከራፊያ (ቃጫ) ወይም ከዋክስ ፕሪንት (ከሰም) የተሠራ ረጅም እጅ ያለው ልብስ፣
▫ ረጅም ቡቡ ወይም ከአፍሪካ ጨርቃጨርቅ ጋር የተጣመረ ቡቡ።
ሴት ሠራተኞች የሚከተሉትን መልበስ ይችላሉ፦
▫ ሰፊና በጥልፍ ያጌጠ ቀሚስ፣
▫ ፓኝ ከክብረ በዓል ቦዲ ጋር፣
▫ የአፍሪካ የራስ መጎናጸፊያ።
ትዕዛዙ የመከላከያ እና የደህንነት ኃይሎችና ልዩ የአለባበስ ደንብ ያላቸው የመንግሥት አካላትን አያካትትም።
የደንቡን ተፈጻሚነት የመሥሪያ ቤት ኃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮች እና ዋና ዳይሬክተሮች ይከታተላሉ።
ይህ ተነሳሽነት ካለው ተምሳሌታዊ እሴት ባለፈ፣ የጋቦንን ባህል እና "በጋቦን የተመረቱ" ምርቶችን ለማስተዋወቅ ያለመ ነው። በተጨማሪም በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግሥት ሠራተኞችን በማንቀሳቀስ እንደ ፓኝ፣ ዋክስ ፕሪንት እና ራፊያ ላሉ የሀገር ውስጥ ጨርቃጨርቅ ምርቶች ያለውን ፍላጎት ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
ቪዲዮው ከ "ግላም አፍሪክ 2026" የፋሽን ትርኢት የተወሰዱ የጋቦን አልባሳትን ያሳያል
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X