ቦትስዋና በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ የቅብብሎሽ ውድድር 'ታሪካዊ' ድል አስመዘገበች
18:32 04.05.2026 (የተሻሻለ: 18:40 04.05.2026)

ሰብስክራይብ
ቦትስዋና በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ የቅብብሎሽ ውድድር 'ታሪካዊ' ድል አስመዘገበች
ቦትስዋና በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ የቅብብሎስ ውድድር ላይ በወንዶች 4x400 ሜትር የፍፃሜ ውድድር "የሀገሪቱን ክብረ ወሰን፣ በቅብብሎሽ ውድድር ታሪክ ፈጣኑን ሰዓት እና በታሪክ ሦስተኛውን ፈጣን ውጤት" ማስመዝገቧን የውድድሩ ይፋዊ ድረ-ገጽ አስታውቋል።
የቦትስዋና የመጀመሪያው ዙር ተወዳዳሪ ሊ ኢፒ "እኛ የፈለግነው የዓለም ክብረ ወሰን መስበር ነበር፤ ስለ ወርቁ ግድ አልነበረንም" ብሏል።
የቀዳሚዎቹ ቡድኖች ውጤት፦
ቦትስዋና — 2:54:47
ደቡብ አፍሪካ — 2:55:07
አውስትራሊያ — 2:55:20
"ይህ ስኬት ለቦትስዋና ሪፐብሊክ ታላቅ ክብርን እና ዓለም አቀፍ እውቅናን አምጥቷል" ሲል የሀገሪቱ መንግሥት ተናግሯል።
ℹ በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ የቅብብሎሽ ውድድር ለዓለም ሻምፒዮና እንደ ማጣሪያነት ያገለግላል። የ2026ቱ ውድድር በጋቦርኔ በሚገኘው የቦትስዋና ብሔራዊ ስታዲየም እየተካሄደ ይገኛል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X