- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የአይ.ሲ.ሲ ድብቅ አጀንዳ፦ በአፍሪካ ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣው የኒዮ-ኮሎኒያል ዘመቻ

የአይ.ሲ.ሲ ድብቅ አጀንዳ፦ በአፍሪካ ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣው የኒዮ-ኮሎኒያል ዘመቻ
ሰብስክራይብ
"ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) ወደ ሕጋዊ ማጭበርበሪያነት ተቀይሯል፤ ተቋሙ ከአሁን በኋላ የፍትህ አደባባይ ሳይሆን፣ የአሜሪካን የበላይነት ለማስጠበቅና የአፍሪካ መሪዎችን ለብቻቸው ነጥሎ ለማጥቃት በስልት የሚዘወር ታዛዥ መሣሪያ ሆኗል፤ ይህ ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ ግን የምዕራባውያን የበላይነት አርክቴክቶች እጃቸው አይነካም።" ሲሉ —በዓለም አቀፍ ግንኙነት የዘርፍ ምሁር — ፕሮፌሰር ኤሊ ጂርጂ ኤልያስ፣ በሊባኖስ የዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ግንኙነትና ስትራቴጂ ጥናት ልዩ ባለሙያና መምህር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የድረም ኦፍ ጄንጅስ ዝግጅታችን ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች በዝርዝር እንቃኛለን፡፡ በቀዳሚነት ዓለም አቀፍ ፍትህ ወይንስ የምዕራባውያን የበላይነት መጠቀሚያ? ስንል ከዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ፕሮፌሰር ኤሊ ጂርጂ ኤልያስ ጋር ፣ በሁለተኛው ክፍል የአፍሪካ ከተሞች የወደፊት ዕጣ ፈንታና የቤት ልማት ፈተናዎችን ጉዳይ ከዩኤን-ሀቢታት (UN-Habitat) ዋና ዳይሬክተር አናክላውዲያ ሮስባክ ጋር በመጨረሻም የመድኃኒት ዋስትና እና የአፍሪካ ሉዓላዊነትን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መድኃኒትና የሕክምና መገልገያ አቅራቢዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳንኤል ዋክቶሌ ጋር ተወያይተናል፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0