አሜሪካ ኢራን ላይ ጦርነት የከፈተችው ስሁት ግምት እና የደህንነት መረጃ ላይ ተመርኩዛ ነው - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
15:10 01.04.2026 (የተሻሻለ: 15:29 01.04.2026)

ሰብስክራይብ
አሜሪካ ኢራን ላይ ጦርነት የከፈተችው ስሁት ግምት እና የደህንነት መረጃ ላይ ተመርኩዛ ነው - ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
ዩናይትድ ስቴትስ የኢራንን ወታደራዊ ኃይል እንዲሁም የመንግሥት ሥርዓት አደረጃጀት በአግባቡ አልተረዳችም ሲሉ የፓለቲካ ጉዳዮች ተንታኙ ዳያሞ ዳሌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
“ይሄ ሁሉ መሪ ሞቶ ሌላ ሀገር ቢሆን እስካሁን ፈርሷል፡፡ ነገር ግን የዕዝ ሰንሰለቱ ምንም አልተነካም፡፡”
በተቃራኒው የኢራን ሕዝብ አርበኝነት ይበልጥ አይሏል ሲሉም ባለሙያው አክለዋል፡፡ ጦርነቱ ከቀጠለም በአሜሪካ የውስጥ ፖለቲካ እንዲሁም በምዕራባውያን መካከል ያለውን ልዩነት ይበልጥ እንደሚያሰፋ አብራርተዋል፡፡
በሌላ በኩል ኢራን በአዲሱ የባለብዙ ዋልታ ዓለም ቀረጻ ላይ የምታደርገው ተሳትፎ አሜሪካ ጦሯን እንድትቀስርባት ካደረጉ ምክንያቶች እንዱ እንደሆነ ተንታኙ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
“ኢራን ለአሜሪካ ተገዳዳሪ ከመሆን አልፋ ብሪክስ ውስጥ ገብታ ከሩሲያና ቻይና ጋር ያላት የባለብዙ ዋልታ ዓለም የመፍጠር አቋሟ አንድ። እስራኤል ላይ ያላት አቋም ሁለት። በእነዚህ ምክንያቶች ኢራንን የኢኮኖሚ እና ወታደራዊ አቅም የማሳጣት...ዓላማ ያለው ጦርነት ነው።”
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X