ግዕዝ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሃሳብ ልውውጥ ላይ ጉልህ ሚና እንደነበረው የሚጠቁም ጥናት ይፋ ሆነ

ግዕዝ
ግዕዝ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.03.2026
ሰብስክራይብ
ግዕዝ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሃሳብ ልውውጥ ላይ ጉልህ ሚና እንደነበረው የሚጠቁም ጥናት ይፋ ሆነ

ይህ አዲስ ጥናት የአርመን ፊደላት ከግዕዝ ጋር ከፍተኛ መዋቅራዊ ተመሳሳይነት እንዳላቸው አሳይቷል፡፡

በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት የሳን ዲዬጎ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በሰው ሠራሽ አስተውህሎት ያከናወኑት ምርምር የአርመን የፊደል አጻጻፍ ሥርዓት ከጥንታዊው የኢትዮጵያ ግዕዝ ፊደላት ጋር እጅግ የላቀ መዋቅራዊ ዝምድና እንዳለው ይፋ አድርጓል፡፡

ተመራማሪዎቹ 28 ሺህ የግዕዝ ሆሄያትን በመጠቀም ባሠለጠኑት የኮምፒውተር ሞዴል፤ የአርመን ፊደላት ከላቲን እና ከሌሎች የካውካሰስ ጽሕፈቶች ይልቅ ለግዕዝ እጅግ የቀረቡ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።


"የጥናቱ ዓላማ በዓይን ከሚታይ ግምት ባለፈ በሒሳባዊ ቀመሮች የተደገፈ ተጨባጭ መረጃ ማቅረብ ነው" ሲሉ የጥናቱ መሪ የሆኑት ሳም ካሴኝ ተናግረዋል፡፡


ከግኝቱ አስደናቂ የሆነው ጉዳይ የአርመን ፊደላት ከግዕዝ ጋር ያላቸው ተመሳሳይነት ግዕዝ ከቀደመው ቅጂው ጋር ካለው ተመሳሳይነት ጋር በጣም የተቀራረበ መሆኑ ነው ያሉት ተመራማሪዎቹ፤ ይህም ተመሳሳይነቱ የአጋጣሚ ላይሆን እንደሚችል የሚጠቁም ነው ሲሉ በፊዚክስ ኦርግ ድረ-ገጽ ላይ ባሳተሙት ጥናት ገልጸዋል።

ይህ ግኝት በአፍሪካ እና በካውካሰስ ሥልጣኔዎች መካከል የነበረውን ጥንታዊ የባሕል እና የዕውቀት ልውውጥ በአዲስ መልክ ለመረዳት ትልቅ ፋይዳ አለው ተብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0