ኢትዮጵያዊው ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ በቤጂንግ የግል የሥዕል ኤግዚቢሽኑን አቀረበ

ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ
ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.03.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያዊው ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ በቤጂንግ የግል የሥዕል ኤግዚቢሽኑን አቀረበ

ሰዓሊው በቻይና ቤጂንግ በሚገኘው ‘ሬድ ብሪክ’ የሥነ-ጥበብ ሙዚየም “ፕራይሞርዲያል ፓዝስ” የተሰኘ የግል የሥዕል ኤግዚቢሽኑን ለዕይታ አቅርቧል።

ስደት፣ መፈናቀል እና ባhhላዊ ማንነትን የሚዳስሱ እንዲሁም የሰውን ልጅ ተጋላጭነት እና ጥንካሬ በሥነ-ጥበባዊ መንገድ የሚገልፁ ከ2019 ጀምሮ የተሳሉና ከ60 በላይ የሚሆኑ ስዕሎች ቀርበዋል።


ሰዓሊ ተስፋዬ፤ "ደካማ ጎንን እና ያለፉባቸውን ገጠመኞች በግልጽ፣ በኃላፊነት እና በልበ ሙሉነት ማቅረብ በራሱ ትልቅ ክብር ነው" ሲል ሰለሥራዎቹ አብራርቷል።


ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0