የሩሲያ ኦርኬስትራ በኬፕ ታውን የጃዝ ፌስቲቫል ታላቅ አድናቆት ተቸረው

ሰብስክራይብ

የሩሲያ ኦርኬስትራ በኬፕ ታውን የጃዝ ፌስቲቫል ታላቅ አድናቆት ተቸረው

ታዋቂው ሩሲያዊ ሙዚቀኛ ኢጎር ቡትማን እና የሞስኮ ጃዝ ኦርኬስትራ አርብ እና ቅዳሜ በተካሄደው የኬፕ ታውን ዓለም አቀፍ የጃዝ ፌስቲቫል ላይ የመጀመሪያ ሥራቸውን አቅርበዋል።

ባንዱ የሩሲያን ጨምሮ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ሥራዎችን በማቀናበር የተለያዩ ሙዚቃዎችን አቅርቦ ከታዳሚው ሞቅ ያለ ምላሽ አግኝቷል።

ቡትማን ለሚዲያ በሰጠው መግለጫ ዝግጅቱንና የታዳሚው አቀባበል በማሞካሸት፤ "አፍሪካውያን የጃዝ ሙዚቃን ምን ያህል እንደሚረዱ እና እንደሚያደንቁ" ያሳያል ብሏል።

ℹ እ.ኤ.አ በ2000 የተጀመረው የኬፕ ታውን ዓለም አቀፍ የጃዝ ፌስቲቫል፤ ተሰጥኦ ያላቸው አፍሪካውያን የጃዝ ሙዚቀኞች ዓለም አቀፍ እውቅና ካገኙ አርቲስቶች ጋር አብረው እንዲሠሩ መድረክ የመፍጠር ዓላማ አለው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0