- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

ከሰንሰለት እስከ ስርአት፡- ያልተቋጨው የባርነት ታሪክ

ከሰንሰለት እስከ ስርአት፡- ያልተቋጨው የባርነት ታሪክ
ሰብስክራይብ

‘‘… እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ የተፈጥሮ ማዕድናት ያሏት አህጉር ፤ አሁንም ድረስ የቅኝ ግዛትና የባዕዳን የንግድ ሥርዓቶችን እንድትከተል መገደዷ በጣም ያሳዝናል።[…]ምክንያቱም እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ አፍሪካ ገና ከቅኝ ግዛት የኢኮኖሚ ጥቃትና ጭቆና እንዳልነቃች ነው የምትቀሳቀሰው። ይህ ለኔ ከዚሁ አህጉር የሚወጡ ሰዎችን ሌሎች የዓለም ክፍሎችን ለማበልጸግ በጉልበት ሠራተኝነት ከሚጠቀምበት ሥርዓት ጋር ቀጥተኛ ትስስር አለው። ይህ ሥርዓት ዛሬም ድረስ በግልጽ እየተሠራ ነው። ለምሳሌ የተፈጥሮ ማዕድኖቻችን አሁንም ከአህጉሪቱ ተነቅለው ወደ ሌላ አገር ሄደው ይመረታሉ፤ ከዚያም ተመልሰው ለእኛው ይሸጡልናል።" ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር እና የአፍሪካ ነፃነትና የጥቁር ሕዝቦች ንቃት አቀንቃኝ ዛንዲሲዌ ራዴቤ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ዓለም በመጋቢት 25 ቀን እ.ኤ.አ የሚዘክረው ዓለም አቀፍ የባርነት እና የአትላንቲክ ባሪያ ንግድ ሰለባዎች መታሰቢያ ቀን ምክንያት አድርገን የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር እና የአፍሪካ ነፃነትና የጥቁር ሕዝቦች ንቃት አቀንቃኝ ዛንዲሲዌ ራዴቤ ጋር ተወያይተናል። ስለ ባርነት የሚተረከውን ታሪክ የሚቀርጸው ማን ነው? እነዚህ ታሪኮችስ በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም ላለው የእኩልነት ማጣት፣ ለኢኮኖሚያዊ ጥገኝነት እና ለስልጣን መዋቅሮች ያላቸው ተጽዕኖስ ምንድነው? የሚሉ ጥያቄዎችን በስፋት ዳስሰናል ።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0