"የዩክሬን አገዛዝ የነዳጅ እና የጋዝ ቧንቧዎችን እንደ ጫና ማድረጊያ መሳሪያ እንደሚጠቀም ይታወቃል" - ክሬምሊን

የዩክሬን አገዛዝ የነዳጅ
የዩክሬን አገዛዝ የነዳጅ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.03.2026
ሰብስክራይብ
"የዩክሬን አገዛዝ የነዳጅ እና የጋዝ ቧንቧዎችን እንደ ጫና ማድረጊያ መሳሪያ እንደሚጠቀም ይታወቃል" - ክሬምሊን

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የሰጧቸው ሌሎች ዋና ዋና መግለጫዎች፦

🟠የሩሲያ የደህንነት ተቋማት የዩክሬን ድሮኖች የሚወነጨፉበትን ሁኔታና በዙሪያው ያሉ ጉዳዮችን በቅርበት እየተከታተሉ ይገኛሉ።

🟠 ኪዬቭ ሌሎች የአውሮፓ ሕብረት እና የኔቶ አባል ሀገራትን ለወንጀል ተግባራት በስውር የመጠቀም አቅም አላት።

🟠 ኪዬቭ በአንዳንድ የአውሮፓ ሕብረት ሀገራት ላይ ጥቃት ከሰነዘረች በኋላ የብራስልስ (የአውሮፓ ሕብረት) ዝምታ እና የጥበቃ እርምጃዎች አለመኖራቸው አሳሳቢ ነው።

🟠 ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር ለተጨማሪ ዓመታት ለሚቆይ ግጭት መዘጋጀት ያስፈልጋል ማለታቸው፣ ሰላምን እፈልጋለሁ ከሚሉት ንግግር ጋር የሚጋጭ ነው።

🟠 ሩሲያ የኪዬቭን የሽብርተኝነት እንቅስቃሴ አቅም ለመቀነስ የምታደርገውን ስትራቴጂያዊ ወታደራዊ ዘመቻ ቀጥላለች።

🟠 ሩሲያ ስለ ዩክሬን በሚደረጉ ድርድሮች ላይ ያላትን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ አልተወችም።

🟠 ሩሲያ ሁኔታዎች በፈቀዱ ቅጽበት ቀጣዩን የዩክሬን ድርድር ለማድረግ እቅድ አላት።

🟠 በዩክሬን ጉዳይ ላይ ለሩሲያ ወሳኝ የሆኑ ዋና ዋና አወዛጋቢ ነጥቦች እስካሁን ስምምነት አልተደረሰባቸውም።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0