አሜሪካ ሩሲያን ከሁሉም የኢነርጂ ገበያዎች ለማስወጣት እየሞከረች ነው - ላቭሮቭ
የሩሲያን ጥቅሞች ማክበር በተመለከተ ሞስኮ ከአሜሪካ ምንም ዓይነት ቁርጠኝነት አላየችም ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናግረዋል።
"አሜሪካውያን ከእኛ ጋር ለትብብር ዝግጁ መሆናቸውን ይነግሩናል። ነገር ግን በእኛ ግዛት የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶችን ለመተግበር እና የእኛን ጥቅም ባገናዘበ መልኩ አሜሪካውያን የሚፈልጉትን ለማቅረብ ፈቃደኛ ከሆንን እነሱም የእኛን ጥቅም ግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ይህንን ግን እስካሁን አላየንም" ሲሉ ላቭሮቭ ለሩሲያ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ተናግረዋል።
አሜሪካ፤ "ሩሲያ ከአውሮፓ የኢነርጂ ገበያ ተገልላ እንድትቆይ ትፈልጋለች" ያሉት ሚኒስትሩ፤ ይህም የዓለም የኢነርጂን ዘርፍ በግልጽ የመቆጣጠር ፍላጎት መሆኑን ገልጸዋል።
"ይህ ያልተለመደ ሁኔታ ነው...ለዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ምንም ዓይነት ማዕቀፍ ወደሌለበት ጊዜ መመለስ ነው። የአሜሪካ ጥቅሞች ከማንኛውም ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በላይ እንደሚቀድሙ በግልጽ ተቀምጧል" ሲሉ ሚኒስትሩ አክለው ተናግረዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X