አንጋፋው አሜሪካዊ የፊልም ተዋናይና የማርሻል አርት ሻምፒዮን ቸክ ኖሪስ በ86 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተዘገበ

ቸክ ኖሪስ
ቸክ ኖሪስ  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.03.2026
ሰብስክራይብ
አንጋፋው አሜሪካዊ የፊልም ተዋናይና የማርሻል አርት ሻምፒዮን ቸክ ኖሪስ በ86 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተዘገበ

ተዋናዩ፣ በብሩስ ሊ “ዘ ዌይ ኦፍ ዘ ድራገን” ፊልም እና “ዎከር፣ ቴክሳስ ሬንጀር” በተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ከፍተኛ ዝናን አትርፏል፡፡

የቀድሞው የዓለም የካራቴ ሻምፒዮኑ፣ የማርሻል አርት ክህሎቱን በመጠቀም በዝቅተኛ ወጪ የተሰሩ ነገር ግን ከፍተኛ የገቢ ስኬት ያስመዘገቡ የድርጊት (አክሽን) ፊልሞች ኮከብ ነበር።


ቤተሰቦቹ በማኅበራዊ ሚዲያ ባስተላለፉት መልዕክት ኖሪስ ሐሙስ ዕለት ሕይወቱ ማለፉን በመግለጽ፣ “የሞቱን ነገር በምሥጢር መያዝ ብንሻም፣ በቤተሰቦቹ ተከቦ በሰላም ማለፉን እንድታውቁልን እንወዳለን” ብለዋል፡፡


ኖሪስ በ1960ዎቹ መገባደጃ ላይ ተከታታይ የካራቴ ሻምፒዮናዎችን አሸፏል፡፡ “ኢንቬዥን ዩ.ኤስ.ኤ” እና “ዘ ዴልታ ፎርስ” ያሉ በርካታ ድርጊት የተሞላባቸው ፊልሞችን ሰርቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0