- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል።አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

በአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነትን የመቀዳጀት ትርጉም እና አስፈላጊነት - መልከ ብዙው ትግል

በአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነትን የመቀዳጀት ትርጉም እና አስፈላጊነት - መልከ ብዙው ትግል
ሰብስክራይብ
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ያለጠው እውነታ ቢኖር አፍሪካ ዛሬም ድረስ የመድኃኒት አቅርቦት ፍላጎቷ በምዕራባውያን መድኃኒት አቅራቢ ኩባንያዎች በጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ነው።

“የምዕራቡ ዓለም የአፍሪካን የሕዝብ ቁጥር ለመቀነስ ከሚፈልግባቸው ምክንያቶች መካከል ዘረኛ ፖሊሲው አንደኛው ነው [...] ሌላኛው ምክንያት ደግሞ ብዙ ወጣት ትውልድ ያላት አፍሪካ የዓለምን ሀብት ለመቆጣጠር ለያዙት ግብ እንቅፋት ትሆናለች የሚል ነው [...] ብሪክስ አፍሪካ ስለአፍሪካ የምታስብበት ብሎም አፍሪካ የራሷን ጥቅም ማስጠበቅ የምትችልበት ጠንካራ ህብረት ነው” ሲሉ የበርካታ ሽልማቶች አሸናፊ ደቡብ አፍሪካዊቷ የማህበረሰብ ጤና ባለሞያ ዶ/ር ሻኪራ ቹናራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ትንቅራችን በአፍሪካ የጤና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አጣዳፊ ጉዳይ ስለመሆኑ ያስቃኘናል። በዚህ ጉዳይ ላይ ደቡብ አፍሪካዊቷ የበርካታ ሽልማቶች አሸናፊ እና የማህበረሰብ ጤና ባለሞያዋ ሻኪራ ቹናራን አነጋግረናል። ተከታዩ ጥንቅራችን ደግሞ፣ በአፍሪካ ሌላኛውን የሉዓላዊነት ገፅታ ያስቃኘናል። በዚህ ጉዳይ ላይ አቶ ምስጋናው እያሱ፣ በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የአየር ንብረት ፋይናንስ አማካሪ እንዲሁም ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ፣ በአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የሰማያዊ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርገናል ።
ሙሉ መረጃ ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0