- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

ሂፕ-ሆፕ (Hip hop) በሀገርኛ፡- የራስ ማንነትን በመገንባት ከውጭ ተፅዕኖ መላቀቅ

ሂፕ-ሆፕ (Hip hop) በሀገርኛ፡- የራስ ማንነትን በመገንባት ከውጭ ተፅዕኖ መላቀቅ
ሰብስክራይብ
''የራሳችን ማንነትና መገለጫ ያለው ሙዚቃ ነው የሚያስፈልገን። ለዚህ ደግሞ አስገራሚ ሀገር በቀል እውቀት፣ ባህልና ጥበብ ያላቸው ሰዎች አሉ። በውጩ ዓለም እየተሳደቡ የራፕ ሙዚቃ የሚዘፍኑ አሉ፣ ስለዚህ እኛ እርሱን በፍፁም አናበረታታም — ጋሽ ሙላቱ አስታጥቄ ኢትዮ ጃዝን እንደፈጠረ ሁሉ፣ እኛም ኢትዮጵያዊ ቀለም ያለው የጥቁር ምት (Black Note) መፍጠር ነው ዓላማችን። አሁን ላይ ሙዚቃዎችን ስንሰራ ጥንታዊ መሠረቶች የሆኑት ቀርቶ፣ ፉከራና ሽለላን ለማካተት እንሞክራለን'' ሲሉ የሙዚቃ አቀናባሪዉ እና ፕሮዲውሰሩ ሁንአንተ ሙሉ (ሁኔ) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ሁለት ጉዳዮችን በምንወያይበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የኢትዮጵያ የሂፕ- ሆፕ ሙዚቃ ጠንካራ ሀገራዊ መሠረት በመጣል እንዴት ከምዕራባዊያን ተፅዕኖ መላቀቅና የራሱን ዘውግ መፍጠር እንደሚችል የሙዚቃ አቀናባሪ እና ፕሮዲውሰርና ሁንአንተ ሙሉ(ሁኔ) ጋር ተወያይተናል። በክፍል 2 ደግሞ ድንበር ተሻጋሪ ትብብር እና ፈጣራን መሠረት በማድረግ በደቡባዊ ዓለም ሀገራት ውስጥ የሠው ሠራሽ አስተውሎት ምርምርና ትግበራን በሚመለከት የቴክኖሎጂ እና ሠው ሠራሽ አስተውሎት ባለሙያ ሥርጉት አለሙ ጋር ቃኝተነዋል።

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0