ጋና የገበያ ሁኔታውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለኮኮዋ አምራቾች ድጋፍ ልታደርግ ነው
17:01 13.02.2026 (የተሻሻለ: 17:04 13.02.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ጋና የገበያ ሁኔታውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለኮኮዋ አምራቾች ድጋፍ ልታደርግ ነው
የጋና ቀድሞ የነበረው የኮኮዋ መግዣ ዋጋ በአንድ ቶን 58,000 የጋና ሴዲ ($5,300 ዶላር) መሆኑ፣ የዓለም አቀፍ ነጋዴዎችን ፍላጎት እንዲቀንስ ማድረጉንና አርሶ አደሮችም ያለ ክፍያ እንዲቀሩ ማድረጉን የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።
እንደ ጋና የፋይናንስ ሚኒስትር ካሲኤል አቶ ፎርሰን ገለጻ፣ አዲሱ የዋጋ ተመን እስከ ጎርጎሮሳውያኑ 2025/2026 የምርት ዘመን ድረስ በአንድ ሜትሪክ ቶን 41,392 ሴዲ (3,580 ዶላር) ሆኖ እንዲስተካከል ተደርጓል።
የጋና ካቢኔ የሀገሪቱ የኮኮዋ ተቆጣጣሪ ተቋም (ኮኮቦድ)፣ በዋጋው መዋዠቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው አርሶ አደሮች በአስቸኳይ ክፍያ እንዲፈጽም መመሪያ ሰጥቷል ሲሉ ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X