ሩሲያ እየተገነባ ባለው ባለብዙ ዋልታ ዓለም ሥርዓት ውስጥ መብቷን እያስከበረች ነው - ላቭሮቭ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ እየተገነባ ባለው ባለብዙ ዋልታ ዓለም ሥርዓት ውስጥ መብቷን እያስከበረች ነው - ላቭሮቭ
ሩሲያ እየተገነባ ባለው ባለብዙ ዋልታ ዓለም ሥርዓት ውስጥ መብቷን እያስከበረች ነው - ላቭሮቭ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.02.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያ እየተገነባ ባለው ባለብዙ ዋልታ ዓለም ሥርዓት ውስጥ መብቷን እያስከበረች ነው - ላቭሮቭ

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር፤ ሩሲያ የምዕራባውያን ሀገራትን ጫና ተቋቁማ በዓለም አቀፍ መድረክ ሕጋዊ ጥቅሟን ማስከበሯን ቀጥላለች ብለዋል። የዓለም ሥርዓት ከፍተኛ ለውጥ እያደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ሞስኮ በዓለም አቀፍ ሕግ እና በሉዓላዊ እኩልነት መርህ ላይ ተመስርታ እየተንቀሳቀሰች ነው ሲሉም አክለዋል።

ዋና ዋና መግለጫዎች፦

◻ ዓለም ለብዙ ዓመታት ሊቆይ የሚችል ፈጣን እና ጥልቅ የለውጥ ምዕራፍ ውስጥ ገብታለች።

◻ ሩሲያ ጠንካራ የውጭ ጫና እየደረሰባቸው ካሉት የቬንዙዌላ እና የኩባ ሕዝቦች ጋር ያላትን አጋርነት ታረጋግጣለች፤ ድጋፍ ለመስጠትም ዝግጁ ነች።

◻ አሜሪካ የኒው ስታርት ስምምነት ገደቦችን እስካከበረች ድረስ ሩሲያ በስምምነቱ ላይ የተቀመጠው እገዳ ጸንቶ እንደሚቆይ ትገነዘባለች።

◻ የግሪንላንድ መሬት ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውል ከሆነ እና ከሩሲያ በታቃራኒ ጥቅም ላይ ከዋለ፤ ሞስኮ ተመጣጣኝ ወታደራዊ-ቴክኒካዊ እርምጃዎችን በመውሰድ ምላሽ ትሰጣለች።

◻ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የአሜሪካ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ በአላስካው ስብሰባ በዩክሬን ጉዳይ ዙሪያ ስምምነቶች ላይ ደርሰው ነበር።

◻ ሩሲያ የልዩ ወታደራዊ ዘመቻውን ግቦች እና ዓላማዎች ለማሳካት ሁሉንም ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ትጠቀማለች።

◻ ሩሲያ የኩርስክ ክልልን ከዩክሬን ታጣቂዎች ነጻ ለማውጣት ሰሜን ኮሪያ ላደረገችው ድጋፍ ምሥጋናዋን ትገልጻለች።

◻ የሩሲያ እና ቻይና ግንኙነት ዓለም አቀፉን ሥርዓት የማረጋጋት ሚና አለው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0