ስንዴ፣ ማዳበሪያ፣ ተስፋ ሰጪ ስምምነቶች እና የደህንነት ድጋፍ - በኒያሜ የሚገኙት የሩሲያ አምባሳደር ስለ ሩሲያ-ኒጀር ግንኙነት የሰጡት መግለጫ
ስንዴ፣ ማዳበሪያ፣ ተስፋ ሰጪ ስምምነቶች እና የደህንነት ድጋፍ - በኒያሜ የሚገኙት የሩሲያ አምባሳደር ስለ ሩሲያ-ኒጀር ግንኙነት የሰጡት መግለጫ
ለኒጀር የተላከ 20 ሺህ ቶን የሩሲያ ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ቶጎ በሚገኘው የሎሜ ወደብ መድረሷን በኒጀር የሩሲያ አምባሳደር ቪክቶር ቮሮፓዬቭ ለሚዲያ ገልጸዋል።
በጎርጎሮሳዊያኑ 2025 ሞስኮ 350 ቶን የሱፍ አበባ ዘይት እና 20 ሺህ ቶን ስንዴ ለኒጀር ማድረሷንም አክለው ገልጸዋል።
ሩሲያ ሌሎች የሳሕል ሀገራት ጥምረት አባላትንም በንቃት ትደግፋለች። እ.ኤ.አ. በታህሳስ 2024 ሞስኮ ከ60 ሺህ ቶን በላይ ስንዴ ለማሊ አቅርባለች።
የቪክቶር ቮሮፓዬቭ ሌሎች ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 የሩሲያ-ኒጀር ትብብር "በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው፡፡" በኢነርጂ፣ በማዕድን ቁፋሮ እና በማቀነባበር ዘርፎች ላይ በርካታ ስምምነቶች በመዘጋጀት ላይ ናቸው።
🟠 ሩሲያ በሳሕል ቀጣና በተለይም በኒጀር ደህንነትን ለማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገች ትገኛለች፤ በተለይም የኒጀርን ወታደራዊ እና የደህንነት ኃይሎች በማሰልጠን ረገድ የጎላ ሚና አላት።
🟠 የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የ"አፍሪካ ኮርፕስ" ወታደሮች ባለፈው ሳምንት በኒያሜ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የተሰነዘረውን የሽብር ጥቃት በመመከት ረገድ ትልቅ ሙያዊ ብቃት አሳይተዋል። እነዚህ ኃይሎች የኒጀርን የመከላከል አቅም በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው።
በቪዲዮው ላይ ለማሊ የተላከ የሩሲያ ስንዴ ኮናክሪ ወደብ ሲደርስ (ታህሳስ 2024)።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X