- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የዲጂታል ሽግግር፦"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" በተግባር

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የዲጂታል ሽግግር፦"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" በተግባር
ሰብስክራይብ
"በኢትዮጵያ ፖስት ረገድ ላደንቀው የምፈልገው ነገር ቢኖር የአገልግሎት ምዝገባ ሂደቱን ነው። [...] የቨርቹዋል ሳጥን ተጠቃሚ ለመሆን የፋይዳ መታወቂያን መጠቀም ይቻላል፤ ከዚያም ሁሉም መረጃዎች ከፋይዳ ሥርዓት በቀጥታ ይሞላሉ። በመቀጠልም በተሳሰሩ የክፍያ መድረኮች አማካኝነት ክፍያ ይፈጸማል። በአንድ ወይም በሁለት ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የራሳችን የሆነ ቨርቹዋል ሳጥን እንዲኖረን ያስችለናል።" ሲሉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደር እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ባለሙያ አቶ እስክንድር መስፍን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ የሁለት ክፍል ዝግጅታችን፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደር እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ባለሙያ ከሆኑት ከአቶ እስክንድር መስፍን ጋር በመሆን፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ጉልህ የዲጂታል ስራዎች ስለሆኑት "ቨርቹዋል የፖስታ ሳጥን" እና "ፖስት ገበያ" የምንወያይ ሲሆን፤ ከፌይዝ ምካችዋ (ደቡብ አፍሪካ)፣ ሪድሌይ ማካሊኪ ( የታዳሽ ኃይል ማዕከል) እና አቢዮላ አኪኖላ (ናይጄሪያ) ስለ ሃይል ሉዓላዊነት እና የቅኝ አገዛዝ ተፅዕኖን ማስወገድ በተመለከተ በሁለተኛው የዝግጅታችን ክፍል እናስደምጣችኋለን፡፡

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0