- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
Continental Drift' በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የአለም የደቡብን ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚከታተል ፕሮግራም ነው።ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

ፋይዳ በለውጥ መንገድ፡- ዲጂታል ማንነት፣ የመረጃ ሉዓላዊነት እና የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ

ፋይዳ በለውጥ መንገድ፡ ዲጂታል ማንነት፣ የመረጃ ሉዓላዊነት እና የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ "ፋይዳ" ከሙከራ ደረጃ አልፎ አሁን ላይ መላውን ሀገራዊ ሥርዓት እያስተሳሰረ ይገኛል። ባንኮችና የክፍያ ሥርዓቶች ከፋይዳ ጋር መገናኘታቸው የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ትልቅ ዕድል ቢሆንም፣ የዜጎች የግል መረጃ ደኅንነት ለመጠበቅ የተለያዩ ስልቶች እየተተገበሩበት ነው ። "የግል መረጃችሁ በትላልቅ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች እጅ ሆኖ በየትኛው የሕግ ሥልጣን ሥር እንደሚገኝ እንኳን ማወቅ[አይቻልም]፤ ምክንያቱም ይህ የኩባንያዎች ምስጢር ነው። ፋይዳን በሚመለከት ግን አንድ ያደረግነው መልካም ነገር የመረጃ ቅነሳ ወይም 'ዳታ ሚኒማይዜሽን' የተሰኘውን መርህ መከተል ነው ፤ ስለዚህ ስለ አንድ ሰው ብዙ መረጃዎችን አንወስድም።" ሲሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ ዘሚካኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ ፋይዳ እንዴት የዲጂታል ኢኮኖሚው መሠረት እየሆነ ነው? የመረጃ ደኅንነትና ግልጽነትስ እንዴት ይረጋገጣል? የሚሉትን አንጋቢ ጉዳዮች የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ ዘሚካኤል ጋር በጥልቀት እንመረምራለን ።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0