- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030፦ የኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግር ጉዞ

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030፦ የኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግር ጉዞ
ሰብስክራይብ
“እኛ [ኢትዮጵያ] በከፍተኛ ሁኔታ ከውጭ በሚገቡ የዲጂታል ሀብቶች ላይ ጥገኛ ነን። ስለዚህ ውይይታችን ስልታዊ እስከሆነ ድረስ እኔ የምመክረው የራሳችን የሆነ የመረጃ ሉዓላዊነት እንዲኖረን ነው። የመረጃ ሉዓላዊነትን የሚያበረታታ እና የሚሟገት የመረጃ አስተዳደር ፖሊሲ ሊኖረን ይገባል። [ለዚህም] በኢትዮጵያ ውስጥ የመረጃ ኤምባሲዎችን ማቋቋም ያስፈልገናል።” ሲሉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደርና ስትራቴጂ ባለሙያ የሆኑት አቶ እስክንድር መስፍን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት የመጀመሪያው ክፍል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስተዳደርና ስትራቴጂ ባለሙያው እስክንድር መስፍን፣ ታህሳስ 11 ይፋ የሆነውን “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ስትራቴጂ ያብራራሉ። ስትራቴጂው በዲጂታል ክፍያ፣ በሳይበር ደህንነት፣ እና በቀጣናዊ ዲጂታል ውህደት ዙሪያ ያለውን ሚና ከኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ጋር የተያያዙ ዕድሎችን ጨምሮ ይዳስሳሉ። በሁለተኛው ክፍልም በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሐዲስ ዓለማየሁ የባህል ጥናት ተቋም ዳይሬክተር ወንድይፍራው ምህረት(ዶ/ር) ጋር ሀገር በቀል እውቀት መልሶ ማግኘት ለጤና እና ለዘላቂ ልማት ለምን አስፈላጊ ሆነ ስንል እንፈትሻለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0