'ቪዚት አዲስ አበባ' የመዲናዋ የቱሪዝም መለያ (ብራንድ) ሆነ

ሰብስክራይብ

'ቪዚት አዲስ አበባ' የመዲናዋ የቱሪዝም መለያ (ብራንድ) ሆነ

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን የመዲናዋን የቱሪስት መዳረሻዎች በስፋት ማስተዋወቅ የሚችሉ የዲጂታል አማራጮችን ይፋ ማድረጉንም የኮሚሽኑ ዲጂታል አማካሪ ሮቤል መስፍን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"ከተማዋ ያሏትን ሐብቶች ለዓለም መሸጥ የሚያስችል ደጋፊ ምሕዳር ያስፈልጓታል። ለዚህም ለአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን የኮርፖሬት ድረ-ገጽ፣ የጎብኚዎች የድረ-ገጽ አፕሊኬሽን እና የማኅበራዊ ሚዲያዎች ተዋውቀው ወደ ሥራ ገብተዋል" ብለዋል።

አማካሪው የአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ኮሚሽን ካዘጋጀው የመጀመሪያው የቱሪዝም ፎረም ጎን ለጎን ስለ ቪዚት አዲስ አበባ የዲጂታል እና የሕትመት መጽሔትም ነግረውናል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0