ምዕራብ አፍሪካውያን በ2025 ስድስት አዳዲስ የጊነስ ወርልድ ክብረ ወሰኖችን አስመዘገቡ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱምዕራብ አፍሪካውያን በ2025 ስድስት አዳዲስ የጊነስ ወርልድ ክብረ ወሰኖችን አስመዘገቡ
ምዕራብ አፍሪካውያን በ2025 ስድስት አዳዲስ የጊነስ ወርልድ ክብረ ወሰኖችን አስመዘገቡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.12.2025
ሰብስክራይብ

ምዕራብ አፍሪካውያን በ2025 ስድስት አዳዲስ የጊነስ ወርልድ ክብረ ወሰኖችን አስመዘገቡ 

በ2025 ከጋና እና ከናይጄሪያ የተውጣጡ ግለሰቦች ስድስት አዳዲስ የጊነስ ወርልድ ክብረ ወሰኖችን በማስመዝገብ አስደናቂ ዓለም አቀፍ እውቅናን ያገኙ ሲሆን ይህም የቀጣናውን ፈጠራ እና ባሕላዊ ተፅእኖ አጉልቶ አሳይቷል።

ጋና

🟠 ሻሮን ዴዴ ፓዲ (የሥነ-ጥበብ አርቲስት) - በዓለም ላይ ግዙፉን የቅጠል ህትመት ስዕል (54.33 ካሬ ሜትር) በመስራት፤

🟠 አኬ-ሊያም ናና ሳም አንክራህ (ሕጻኑ ሊቅ) - የዓለም ላይ ትንሹ ወንድ ፕሮፌሽናል አርቲስት ተብሎ እውቅና አግኝቷል ( 1 ዓመት ከ152 ቀናት እድሜ)።

ናይጄሪያ

🟠 ሂልዳ ባቺ (ታዋቂ ሼፍ) - ትልቁን የናይጄሪያ ባሕላዊ ጆሎፍ ሩዝ (8,780 ኪሎ ግራም) በማብሰል፡፡

🟠 ካንዬያቹክዉ ታግቦ-ኦኬኬ (አርቲስት) - ግዙፍ የሸራ ላይ ጥበብ በማዘጋጀት፡፡

🟠 አኒታ ናታቻ አኪዴ አካ “ሲምፕሊ ታቻ” (የእውነታ ትዕይንት ኮከብ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ) - በ8 ሠዓታት ውስጥ (82) እና በ24 ሠዓታት ውስጥ (144) ብዙ ከፍተኛ የለውጥ ሜክአፖችን (ሜክኦቨር ሜክአፕ) በመሥራት ሁለት የዓለም ክብረ ወሰን ማዕረጎችን አግኝተዋል፡፡

🟠 ጆሽዋ ኦሉሳንያ (ትራምፔት ተጫዋች) - ረጅም እና ለተከታታይ ሠዓታት ትራምፔት በመጫወት (25 ሠዓታት ከ30 ደቂቃ)።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱምዕራብ አፍሪካውያን በ2025 ስድስት አዳዲስ የጊነስ ወርልድ ክብረ ወሰኖችን አስመዘገቡ
ምዕራብ አፍሪካውያን በ2025 ስድስት አዳዲስ የጊነስ ወርልድ ክብረ ወሰኖችን አስመዘገቡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.12.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0