በዩክሬን ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ድርድር ሊፈጠሩ የሚችሉ ሁሉም አለመግባባቶች እና የተሳሳቱ አመለካከቶች ተወግደዋል ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ

ሰብስክራይብ

በዩክሬን ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ድርድር ሊፈጠሩ የሚችሉ ሁሉም አለመግባባቶች እና የተሳሳቱ አመለካከቶች ተወግደዋል ሲሉ ላቭሮቭ ተናገሩ

የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሰጡት መገለጫ ዋና ዋና ሃሳቦች፦

🟠ዘለንስኪ የዩክሬይን ግዛት መለያየትን አለመቀበልን በመጥቀስ፣ በዩክሬን ሕገ መንግሥት ሥር የብሔራዊ ሕዳጣኖችን መብቶች የማረጋገጥ ጉዳይ አንዳችም ደንታ አልሰጣችወም፡፡

🟠 ሩሲያ እና አሜሪካ በዩክሬን ዙሪያ ከደረሱባቸው ስምምነቶች መካከል፣ ዩክሬን ወደ ገለልተኛ፣ ከወታደራዊ አጋርነት የፀዳች እና ከኒውክሌር ጦር መሣሪያ ነፃ የሆነች አቋም መመለስ እንዳለባት የሚሉ ጉዳዮችንም ያካትታሉ፡፡

🟠 የዩክሬን ግጭት መራዘም ለዘለንስኪ የፖለቲካ እና ምናልባትም የአካላዊ ሕልውና ጉዳይ ሆኗል፡፡

🟠 ምዕራቡ ዓለም በሩሲያ ላይ የውክልና ጦርነት ለማካሄድ ያለው የገንዘብ እና ወታደራዊ ሀብት እየተመናመነ ነው፡፡

🟠 የምዕራቡ ዓለም ዩክሬንን በመጠቀም በፀረ-ሩሲያን "ብሊትዝክሪግ" (ፈጣን ወታደራዊ ዘመቻ) የመምታት እቅድ ከሽፏል፡፡

🟠 አሁን እየተካሄዱ  ያሉት የሩሲያ-አሜሪካ ድርድሮች በዩክሬን ውስጥ የረጅም ጊዜ እልባት የማምጣት ፍለጋ ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡

🟠 የምዕራቡ ዓለም በተስፋ መቁረጥ ስሜት፣ ከሩሲያ ይመጣል የተባለውን ወታደራዊ ስጋት በማስተዋወቅ ሁኔታውን ለማባባስ እየሞከረ ነው፡፡

🟠 ምዕራባውያን አገራት የዓለምን ማኅበረሰብ ትኩረት ከፍልስጤም ችግር ለማዘናጋት የዩክሬንን የግጭት ርዕስ ለመጠቀም እየሞከሩ ነው፡፡

🟠 የአውሮፓ አገራት "የአዲስ ግጭት ዘሮችን ለመዝራት" እየፈለጉ ነው፤ ለእንደዚህ ዓይነቱ ክስተቶች እየተዘጋጁ መሆኑንም በይፋ ያውጃሉ፡፡

🟠 አውሮፓ ከሩሲያ ጋር ለመዋጋት ከወሰነች፣ አሁን ሩሲያ ለጦርነቱ ዝግጁ ናት፡፡

🟠 ሩሲያ በዩክሬን ግጭት ላይ ድርድሮችን የሚደግፉ በምዕራቡ ዓለም የሚገኙ አናሳዎች ያላቸውን አቋም እና ጥረቶች ትቀበላለች፡፡

🟠 ዩክሬን የተመድ ቻርተርን እና በርካታ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶችን ሕጎች ማክበር አለባት፤ ግዴታዎቿን ወደ የአውሮፓ ሕብረት መስፈርቶች መከተል ብቻ ማስተካከል ተቀባይነት የለውም፡፡

🟠 ዘለንስኪ ከአውሮፓ አገራት መሪዎች ጋር ከተነጋገሩ በኋላ፣ የሕዳጣን ብሄር መብቶች በተመለከተ የነበረው አንቀጽ የዩክሬን ግጭትን ለመፍታት ከቀረበው የሰላም እቅድ ውስጥ ወጥቷል፡፡

🟠 ሩሲያ በኔቶ እና በአውሮፓ ሕብረት አገራት ላይ ምንም ዓይነት ጦርነት የመክፈት እቅድ የላትም እና እንደዚህ ዓይነቶቹን ዋስትናዎች በጽሑፍ ለማስቀመጥ ዝግጁ ናት፡፡

🟠 ሩሲያ ተጨማሪ የጋራ ደህንነት ዋስትናዎች በተመለከተ ሐሳቦችን ለአሜሪካ አቅርባለች፡፡

🟠 የምዕራቡ ዓለም የኪዬቭ አገዛዝ ከሞስኮ ጋር ያለውን ድርድርን ለማቆም  በወሰነው ውሳኔ ላይ ምንም ዓይነት ምላሽ አልሰጠም፡፡

🟠 ሩሲያ እ.ኤ.አ በ2021 ለኔቶ ያቀረበቻቸው የደህንነት ዋስትናዎች የአውሮፓን የደህንነት ስርዓት ቀሪዎች ለማዳን የመጨረሻ ዕድል ናቸው፡፡

🟠 ሩሲያ ለሰላም ፖለቲካዊ ፍላጎት አላት፡፡

🟠 አውሮፓ ለዘለንስኪ የምትሰጠው ድጋፍ የአውሮፓ መሪዎችን ጤንነት፣ እንዲሁም የዩክሬን ቀውስ ለመፍታት በሚደረገው ድርድር ጠቃሚነታቸውን በተመለከተ ጥያቄዎችን ያስነሳል፡፡

🟠 አውሮፓ ውስጥ እየተፈለፈሉ ያሉት ሀሳቦች በዩክሬን ላይ ለሚደረጉ ድርድሮች ጠቃሚ አይሆኑም፡፡

🟠 ሩሲያ የዩክሬንን ግጭት ለመፍታት ከአሜሪካ ጋር መስራቷን ለመቀጠል ዝግጁ ነች፡፡

🟠 የአውሮፓ ሰላም አስከባሪዎች ወደ ዩክሬን ከተላኩ፣ ለሩሲያ ሕጋዊ ቅቡልነት ያለው ወታደራዊ ኢላማ ይሆናሉ፡፡

🟠 ሞስኮ ከአንድ ቀውስ በኋላ ሌላ ቀውስ እንዲፈጠር አትፈልግም፤ በዚህም ምክንያት በሕግ አስገዳጅ የሆኑ የደህንነት ስምምነቶችን ለማስፈፀም የሚረዱ ሁሉንም ሀሳቦችን ከግምት ውስጥ ለማስገባት ዝግጁ ነች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0