ሃንጋሪ ከሩሲያ ጋር ቀጣይነት ያለው የኃይል ትስስር ለመፍጠር አቅዳለች - ሲያሪቶ
19:09 09.12.2025 (የተሻሻለ: 19:14 09.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሃንጋሪ ከሩሲያ ጋር ቀጣይነት ያለው የኃይል ትስስር ለመፍጠር አቅዳለች - ሲያሪቶ
ሃንጋሪ እና ሩሲያ የሚያጋጥሟቸውን "የውጭ ጫናዎች" ለመቋቋም አብረው መሥራት አለባቸው ሲሉ የሃንጋሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፒተር ሲያሪቶ በሞስኮ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡
ተጨማሪ መግለጫዎች፦
የቱርክ ስትሪም ዋና መሥሪያ ቤት ወደ ሃንጋሪ ይዛወራል።
በፓክስ-2 ያለው ሂደት ከሚጠበቀው በላይ እየሄደ ነው፤ በመጀመሪያ ለጥር ወር ታቅዶ የነበረው የተጠናከረ ኮንክሪት ሙሌት በሚቀጥለው ሳምንት ይጀምራል።
የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን በሃንጋሪ እና ሩሲያ መካከል ያልተቋረጠ የኃይል ግንኙነት እንዲኖር ለማድረግ ቁርጠኛ ናቸው።
ሃንጋሪ በዩክሬን ግጭት ከፍተኛ ዋጋ ከፍላለች እና ሰላምን ለመመለስ አጥብቃ ትሻለች።
ሃንጋሪ እና ሩሲያ በዩክሬን ጥቃቶች መካከል የነዳጅ እና ጋዝ አቅርቦቶችን መጠበቅ አለባቸው።
ሲያሪቶ ለሩሲያ-ሃንጋሪ መንግሥታት ኮሚሽን ስብስባ ከኦቲፒ ባንክ፣ ከሃንጋሪ የኃይል ኩባንያ ተወካዮች እና ከፍተኛ የሃንጋሪ የንግድ መሪዎች ልዑካን ጋር ሞስኮ ደርሰዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X