- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

የውኃ ነገር፡ በቀጠናዊ አጋርነት እና ሁለንተናዊ አህጉር አቀፍ ትብብር ፍትሃዊ ክፍፍል የሚሻው ውዱ የተፈጥሮ ኃብት

የውኃ ነገር፡ በቀጠናዊ አጋርነት እና ሁለንተናዊ አህጉር አቀፍ ትብብር ፍትሃዊ ክፍፍል የሚሻው ውዱ የተፈጥሮ ኃብት
ሰብስክራይብ

''ውኃ ጥቅም ብዙና ድንበር ተሻጋሪ የተፈጥሮ ኃብት እንደመሆኑ በዋነኝነት አንዳንድ ሀገራት ለግብርና ሲያውሎት፣ አንዳንዶቹ ለሥራ ፈጠራ ዕድል፣ ሌሎቹ ደግሞ ኃይል ለማመንጨት ይጠቀሙበታል — ሀገራት እርስ በርስ በትብብር መሥራት የሚችሉባቸው መሠረቶቹ ሲኖሩ ደግሞ ከውኃ የሚገኘውን ከፍተኛ ኃብት መቋደስ ይችላሉ '' ሲሉ በውኃና መሬት ኃብቶች ማዕከል ምክትል ዳይሬከተሩ ጠና አላምረው (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን የመጀመሪያ ክፍል ፍትሃዊ የውኃ ኃብት ክፍፍል በሀገራት መካከል እንዲፈጠር ቀጠናዊ አጋርነቶች እንዲሁም ሁለንተናዊ አህጉር አቀፍ ትብብር መጠናከር በሚመለከት በውኃና መሬት ኃብቶች ማዕከል ምክትል ዳይሬከተሩ ጠና አላምረው (ዶ/ር) በእንግድነት ጋብዘናቸዋል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ ደቡብ አፍሪካ በብሪክስ አባል ሀገራት ውስጥ ያላትን ቁልፍ ሚና እንዲሁም ስትራተጂካዊ ግንኙነትን በደቡብ አፍሪካ የግብርና ቢዝነስ ምክር ቤት ዋና የምጣኔ ሐብት ባለሙያው ዋንዲሊ ሲህሎቦ ያስረዱናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0