ጋናን በለጋሾች ዶላር ብቻ መገንባት ስለማይቻል በትምህርትና ግብርና ዘርፍ አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ሞዴል ያሻል - ፕሬዝዳንት ማሃማ

ሰብስክራይብ

ጋናን በለጋሾች ዶላር ብቻ መገንባት ስለማይቻል በትምህርትና ግብርና ዘርፍ አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ሞዴል ያሻል - ፕሬዝዳንት ማሃማ

ጆን ድራማኒ ማሃማ ጠንካራ የትምህርት ስርዓት በውጭ ዕርዳታ ላይ ብቻ ሊመሰረት እንደማይችል በመግለጽ፤ ጋና የሀገር ውስጥ ገቢ አሰባሰቧን እንድታሳድግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዓለም አቀፍ ድጋፍ አሁንም ጠቃሚ ቢሆንም፤ ዘላቂ ለውጥ በጋና የራሷ ሀብቶች መደገፍ አለበት ሲሉ በ2025 የዶሃ ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር ተደምጠዋል፡፡

የሀገር ውስጥ መፍትሄዎች እንደሚሠሩ ለማረጋገጥ፤ ከሸቀጦችና አገልግሎቶች ላይ በሚጣል የ2.5 በመቶ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የትምህርት ጉዳዮች የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርገውን የጋና ትምህርት ትረስት ፈንድ ሞዴል ጠቅሰዋል፡፡

አስተማማኝ ውስጣዊ የገንዘብ ድጋፍ የትምህርት ቤት መሠረተ ልማቶችን፣ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ለማሻሻል እና ከፍተኛ ትምህርትን ለማስፋፋት ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ማሃማ ጋና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ከዝናብ ጥገኝነት የተሻገረ ግብርና ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባትም ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ በተመጣጣኝ የመስኖ ልማት፣ አርሶ አደሮችን በመጠበቅ እና ብሔራዊ የምግብ አቅርቦት በማረጋገጥ ምርታማነትን ለማሳደግ ለመጠነ ሰፊ ኢንቨስትመንት ጥሪ አቅርበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0