- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የኢንቨስትመንት ባንክ ዘርፍ አጀማመር በኢትዮጵያ ፡- አዲሱ የፋይናንስ ምዕራፍ ጅማሮ

የኢንቨስትመንት ባንክ ዘርፍ አጀማመር በኢትዮጵያ ፡- አዲሱ የፋይናንስ ምዕራፍ ጅማሮ
ሰብስክራይብ

“የሚሰራ የካፒታል ገበያ ካለህ፤ ገበያው በራሱ የረዥም ጊዜ ብድሮችንና ለዚያ የሚሆኑ ነገሮችን ያቀርባል፡፡ ባንኮች ደግሞ ለአጭር ጊዜ የሚሆኑ ዐይነት ብድሮችን ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ የካፒታል ገበያ በምንፈልገው ደረጃ አለመኖሩን ተከትሎ የሆነ ነው፡፡ ሁሉም ነገር በተለመዱት ባንኮች በኩል እንደሚፈጸም ያሳያል፡፡ አንዳንድ ክፍተቶችም አሉ ፤ ሆኖም ክፍተቶቹ በካፒታል ገበያው የሚፈቱ ይሆናል፡፡” ሲሉ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከፍተኛ አማካሪ አቶ ሲራክ ሰለሞን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅትየኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከፍተኛ አማካሪ ከሆኑት አቶ ሲራክ ሰለሞን ጋር በመሆን ለውጥ ወዳልተለየው ወደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ዘልቀን በማደግ ላይ ያለውን የኢንቨስትመንት ባንክ ጅማሮን እንዳስሳለን፡፡ የካፒታል ገበያው መከፈትና የአዳዲስ የኢንቨስትመንትባንኮች ወደ ስራ መግባት ለባለሀብቶች፣ ለሥራ ፈጣሪዎች እና በአጠቃላይ ለሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ምን ይዞ ይመጣል? ምን አበርከቶ አለው? እድልና ፈተናዎቹስ ምንድናቸው? በሚሉ ጉዳዮች ላይ ቆይታ አድርገናል፡፡

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0