- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የአፍሪካ ጉዞ ከትግል እስከ መታደስ ፡ ታሪክን መመለስና የወደፊቱን መወሰን

የአፍሪካ ጉዞ ከትግል እስከ መታደስ ፡ ታሪክን መመለስና የወደፊቱን መወሰን
ሰብስክራይብ

"አፍሪካ ነጻ አይደለችም። በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ፣ በወታደራዊ ወይንም በሌላ በማንኛውም ነገር ቢሆን፤ የአፍሪካ ነፃነት መጀመር ያለበት ከእውቀት [ጥገኝነት] ነፃነት ነው ።" ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህኛው የ ራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በክፍል አንድ፣ ከፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ጋር የአፍሪካን የትግል ጀግኖች በምዕራባዉያኑ ቦታ የማይሰጣቸውና የተረሱት ለምንድን ነው ስንል እንጠይቃለን ፤ በክፍል ሁለት ደግሞ በአዲስ አበባ በተካሄደው የቻይና–አፍሪካ ግብርና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስብሰባ ላይ ለአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት መጻኢ ተስፋዎቹ እንወያያለን፣ ለዚህም የተ.መ.ድ የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ)ረዳት ዋና ዳይሬክተር እና የአፍሪካ ቀጣናዊ ተወካይ አበበ ኃይለ ገብርኤል (ዶ/ር) ፣ የግብርና ሚኒስቴር ዴኤታ ኤፋ ሙለታ (ዶ/ር) እና የአፍሪካ ህብረት የልማት ኤጀንሲ አዲስ አጋርነት ለአፍሪካ ልማት የኔትዎርክ ማናጀር ፕሮፌሰር ኤሪክ ቻካውያ አነጋግረናቸዋል።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0