- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
Continental Drift' በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የአለም የደቡብን ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚከታተል ፕሮግራም ነው።ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

ከፖሊሲ አውጪነት ወደ ፖሊሲ ተቀባይነት :- በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) የተደቀኑ ፈተናዎች በአፍሪካ

ከፖሊሲ አውጪነት ወደ ፖሊሲ ተቀባይነት :- በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) የተደቀኑ ፈተናዎች በአፍሪካ
ሰብስክራይብ
አፍሪካ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ70 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለእዳ ክፍያ በማውጣት፣ ከጤናና ትምህርት በለጠ የፋይናንስ ጫና ውስጥ ወድቃለች።
" አለምዓቀፉን የገንዘብ ተቋም በተቀበልክ ጊዜ፣ የማክሮ ፖሊሲህን በሙሉ አሳልፈህ ትሰጣለህ። እኔ የማክሮ ኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ነኝ፤ ሁሉንም ፖሊሲዎች አውቃለሁ። ከአይ.ኤም.ኤፍ. ጋር ስምምነት ስትፈጽም፣ የማክሮ ፖሊሲ የመወሰን አቅምህን በጠቅላላ ታጣለህ። የፊስካል ፖሊሲ ታጣለህ፤ የገንዘብ ፖሊሲ ታጣለህ፤ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ታጣለህ። በመሠረቱ ራስን በራስ የማስተዳደር አቅምህን ታጣለህ።" — ሲሉ የማክሮ ኢኮኖሚክስ እና ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የአፍሪካን ዕጣ ፈንታ የሚወስነው ማን ነው? በሚለው ሀሳብ ዙሪያ የማክሮ ኢኮኖሚክስ እና ኢንተርናሽናል ኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ከሆኑት አለማየሁ ገዳ (ዶ/ር) ሰፊ ውይይት አድርገናል፡፡ የኢትዮጵያ የወይን ዘርፍ በአለምአቀፍ ገበያ እንዴት ተወዳዳሪ መሆን ይችላል? የብሪክስና የደቡብ ለደቡብ ትብብሮችስ ምን አይነት እድልና አቅሞች ይፈጥሩለታል ስንል ከወይን ባለሙያ ዳዊት ዳንኤል ጋር ሰፊ ውይይትን አድርገናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
አዳዲስ ዜናዎች
0