የብሪቲሽ አሜሪካን ትምባሆ ኩባንያ በዩናይትድ ኪንግደም ከሚከተለው በተቃራኒ በአፍሪካ የጤና ሕጎችን እየሸረሸር ነው በሚል ክስ ቀረበበት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየብሪቲሽ አሜሪካን ትምባሆ ኩባንያ በዩናይትድ ኪንግደም ከሚከተለው በተቃራኒ በአፍሪካ የጤና ሕጎችን እየሸረሸር ነው በሚል ክስ ቀረበበት
የብሪቲሽ አሜሪካን ትምባሆ ኩባንያ በዩናይትድ ኪንግደም ከሚከተለው በተቃራኒ በአፍሪካ የጤና ሕጎችን እየሸረሸር ነው በሚል ክስ ቀረበበት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.11.2025
ሰብስክራይብ

የብሪቲሽ አሜሪካን ትምባሆ ኩባንያ በዩናይትድ ኪንግደም ከሚከተለው በተቃራኒ በአፍሪካ የጤና ሕጎችን እየሸረሸር ነው በሚል ክስ ቀረበበት

ከዛምቢያ የብሪቲሽ አሜሪካን ትምባሆ ኩባንያ የወጣ አንድ ደብዳቤ መንግሥት የትምባሆ ማስታወቂያ እና ስፖንሰርሺፕ ላይ እገዳ እንዲያነሳ፣ ግራፊክ የጤና ማስጠንቀቂያዎችን እንዲቀንስ እና ለጥሰቶች የሚተላለፉትን ቅጣቶች እንዲያቃልል አሳስቧል ሲል አንድ የእንግሊዝ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

ድርጅቱ ጥብቅ ሕጎች ሕገ-ወጥ ንግድን ሊያሳድጉ ይችላሉ በማለት ከ2020 ጀምሮ በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የታገዱትን እና የተለያዩ ቃና ያላቸው ምርቶች ላይ የተጣሉ ገደቦችን ለማስወገድ ይፈልጋል፡፡

ዛምቢያዊው ተሟጋች ማስተር ቺምባላ ይህንን እርምጃ “ፍጹም ግብዝነት” ሲሉ አውግዘዋል፡፡

“የብሪታንያን ሕዝብ ጥበቃ ይፈቅዳሉ፤ የዛምቢያን ሕዝብ ሞት ያጸድቃሉ” ብለዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በዛምቢያ በየዓመቱ ከ7ሺህ በላይ ከትምባሆ ጋር የተያያዘ ሞት እንደሚመዘገብ ትንበያውን ያስቀምጣል። የዓለም ጤና ድርጅት ባለሥልጣናት በዘርፉ “ዓለም አቀፍ የቁጥጥር እርምጃዎችን ለማዳከም” ጥረቶች እያደጉ መምጣታቸውን በቅርቡ አስጠንቅቀዋል። ተቺዎች የብሪቲሽ አሜሪካን ትምባሆ ጣልቃገብነቶች ህይወትን ሊያሳጡ ይችላሉ ይላሉ።

የብሪቲሽ አሜሪካን ትምባሆ “ተራማጅ ደንብን” እንደሚደግፍ አጥብቆ ቢናገርም፤ ተሟጋቾች ኩባንያው ያቀረባቸው ሀሳቦች “ድንቡን በጣም ስለሚያዳክሙ በህብረተሰቡ ላይ ዘላቂ ለውጥ እንዲያመጣ የሚፈለገው ተጽዕኖ አይሳካም” ሲሉ ይከራከራሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0