የአፍሪካ ልማት ባንክ ለጋና የወጣቶችና ሴቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ 71.55 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት እንደሚያደርግ ተገለፀ
17:35 13.11.2025 (የተሻሻለ: 17:44 13.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለጋና የወጣቶችና ሴቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ 71.55 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት እንደሚያደርግ ተገለፀ
ባንኩ በተለይም በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክልሎች ለሚገኙ ሴቶችና ወጣቶች 28 ሺህ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ላለመው የአራት ዓመት ፕሮግራም ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታውቋል።
ይህ ተነሳሽነት ዲጂታል ክህሎቶች፣ የፈጠራ ኢንዱስትሪዎች፣ ኮዲንግ እና የግብርና ንግድን ጨምሮ ለገበያ ተፈላጊ የሆኑ የክህሎት ሥልጠናዎች ላይ ያተኩራል ተብሏል።
"ይህ ፕሮግራም ጋና የሥነ-ሕዝብ እድገቷን ለውጤት ለመቀየር በምታደርገው ጥረት ሴቶችን እና ወጣቶችን ለገበያ ተፈላጊ ክህሎቶች፣ የፋይናንስ ተደራሽነት እና የኑሮ ዕድሎችን በማስታጠቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል" ሲሉ በጋና የአፍሪካ ልማት ባንክ ሥራ አስኪያጅ ኢየሩሳሌም ፋሲካ ተናግረዋል።
ፕሮግራሙ በተለይም መዋቅራዊ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጋላጭነት ያላቸውን ክልሎች ዒላማ ያደረገ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የክህሎት ልማትን በማሳደግ ዋነኛ ማህበራዊ የግጭት መንስኤዎችን ለመፍታት ያለመ ነው ሲል ባንኩ ገልጿል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X