በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ አውቶብስ ፈጣን መስመር ግንባታ በሚቀጥለው ወር እንደሚጀመር ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ አውቶብስ ፈጣን መስመር ግንባታ በሚቀጥለው ወር እንደሚጀመር ተገለፀ
በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ አውቶብስ ፈጣን መስመር ግንባታ በሚቀጥለው ወር እንደሚጀመር ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.11.2025
ሰብስክራይብ

በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ አውቶብስ ፈጣን መስመር ግንባታ በሚቀጥለው ወር እንደሚጀመር ተገለፀ

በመዲናዋ የመጀመሪያ የሆነውና ከፒያሳ እስከ ጀሞ-3 ኮንዶሚኒየም የሚዘረጋው የኤሌክትሪክ አውቶቡስ ፈጣን መንገድ ኮሪደር ግንባታን በታህሳስ ወር ለማስጀመር መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡

15.64 ኪሎ ሜትር ሽፋን፣ 20 ዘመናዊ ጣቢያዎችን እና 12 ተጨማሪ አገልግሎቶችን የሚይዘው ይህ ፕሮጀክት፤ በሁለት ዓመት ግዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር እያሱ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡

መንገዱ በቀን 400 ሺህ የሚደርሱ መንገደኞችን እንደሚያስተናግድ የሚጠበቅ ሲሆን ወጪው በከተማ አስተዳደሩ እና በአጋር ድርጅቶች ይሸፈናል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0