“ኢትዮጵያ ምድሯም ልጆቿም ሀብታሞች ናቸው እስኪባል ድረስ ለአፍታም አንቆምም” - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
15:59 13.11.2025 (የተሻሻለ: 16:34 13.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
“ኢትዮጵያ ምድሯም ልጆቿም ሀብታሞች ናቸው እስኪባል ድረስ ለአፍታም አንቆምም” - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
4ኛው የማዕድንና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ተከፍቷል፡፡
“ኢትዮጵያ ምድሯ ባለ ሦስት ድርብ ሀብት የያዘ ነው። የከርሰ ምድር ሀብቶች፣ የገጸ ምድር ሀብቶችን እና ልዩ የአየር ንብረትን ታድላለች። መንግሥት የሰጠው ልዩ ትኩረትና የወሰዳቸው እርምጃዎች ለዘርፉ መነቃቃት እና ተስፋን በማምጣት በማዕድን ኢንቨስትመንትና ወጪ ንግድ ከፍተኛ እመርታን ፈጥረዋል” ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ኤክስፖውን በይፋ በከፈቱበት ወቅት ተናግረዋል፡፡
ዓለም አቀፍ ኤክስፖው ባለድርሻ አካላትን፣ ባለሀብቶችን፣ የቴክኖሎጂ አምራቾችን እና ምሁራንን በማሰባሰብ ኢትዮጵያ ያሏትን መልካም ዕድሎች የምታሳይበት እና ተግዳሮቶች በቅንጅት የሚፈቱበት ወሳኝ መድረክ እንደሆነም አክለዋል፡፡
ከህዳር 4 እስከ 7 የሚቆየው ኤክስፖ፤ ዓለም ዓቀፍ የማዕድንና ቴክኖሎጂ አምራቾች እና አቅራቢዎች ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበት ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


