ቦይንግ ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ በተከሰከሰው አውሮፕላን ህይወቷ ላለፈ ወጣት ቤተሰቦች ከ28 ሚሊዮን ዶላር በላይ ካሳ እንዲከፍል ተወሰነበት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቦይንግ ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ በተከሰከሰው አውሮፕላን ህይወቷ ላለፈ ወጣት ቤተሰቦች ከ28 ሚሊዮን ዶላር በላይ ካሳ እንዲከፍል ተወሰነበት
ቦይንግ ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ በተከሰከሰው አውሮፕላን ህይወቷ ላለፈ ወጣት ቤተሰቦች ከ28 ሚሊዮን ዶላር በላይ ካሳ እንዲከፍል ተወሰነበት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.11.2025
ሰብስክራይብ

ቦይንግ ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ በተከሰከሰው አውሮፕላን ህይወቷ ላለፈ ወጣት ቤተሰቦች ከ28 ሚሊዮን ዶላር በላይ ካሳ እንዲከፍል ተወሰነበት

የቺካጎ የፌደራል ፍርድ ቤት የተመድ የአካባቢ ጥበቃ ሠራተኛ ለነበረችው ለሺካ ጋርግ ቤተሰብ የወሰነው ካሳ፤ በ2011 ዓ.ም በኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ በተከሰቱ አደጋዎች ምክንያት ከተመሰረቱ በርካታ ክሶች ውስጥ የተላለፈ የመጀመሪያው ውሳኔ ተደርጎ ተወስዷል፡፡

በትናንትናው ዕለት በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረሰ ስምምነት መሠረት የተጎጂዋ ቤተሰብ 35.85 ሚሊዮን ዶላር ሙሉ የፍርድ መጠን እና 26 በመቶ ወለድ ከቦይንግ ኩባንያ እንደሚከፈለው የቤተሰቡን ጠበቆች ጠቅሰው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

"አብዛኛዎቹን ጥያቄዎች በስምምነት ብንፈታም፤ የተጎጂ ቤተሰቦች በፍርድ ቤት የጉዳት ካሳዎች የመጠየቅ መብት አላቸው፤ እኛም መብታቸውን እናከብራለን" ሲሉ የቦይንግ ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ አንስተዋል።

ℹ ከቀናት በፊት የአሜሪካ ፍትሕ ሚኒስቴር ቦይንግ ላይ ሊቀርብ የነበረ የወንጀል ክስ ውድቅ እንዲደረግ ያቀረበውን ጥያቄ ፍርድ ቤት ማፅደቁ ይታወሳል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0